ካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጲያ በሶዶ ሀገረ ስብከት የኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የእርባታ ፍየሎችን ገዝቶ ለማሰራጨት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጲያ በሶዶ ሀገረ ስብከት የኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መሰረቱን በኢትዮጵያ ያደረገ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ በተለያዩ ቀበሌያት የልማት መርሃ ግብር (ፕሮጄክት) ቀርጾ እየተገበረ ይገኛል።
ስለሆነም ICSP project Attempt for sustainable Economic well-Being (A-SEW ፕሮጀክት አማካኝነት የእርባታ ፍየሎችን ገዝቶ ለማሰራጨት ይፈልጋል።
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለአመቱ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀቶች ቅጂዎች ማቅረብ የምችሉ፣ ቀደም ስል በተመሳሳይ የማቅረብ ልምድ ያላቸዉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የምችሉ ወይም የካምፓኒ ፕሮፋይል ማቅረብ አለባቸዉ።
ስለሆነም።
1. ጨረታው ክፍት በሆነ አሰራር ይፈጸማል።
2. የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 የስራ ቀናት ማለትም ከ 10/9/2018 እስከ 18/9/2018 በካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጲያ የሶዶ ቅ/ ጽ/ቤት በኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በድርጅቱ ስም በኢትዮ. ንግድ ባንክ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000329846109 በማስገባትና የከፈሉበትን የባንክ ገቢ ደረሰኝ በማምጣት ከካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጲያ የሶዶ ቅ/ጽ/ቤት በኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላሉ።
3. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ መጠን 2 % የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ሁሉም ተጫራቾች አንድ ኦሪጅናል ምልክት የተደረገበት “ኦሪጅናል” እና አንድ ቅጂ ልክ እንደ መጀመሪያው በተመሳሳይ መልኩ የተፈረመ እና ርዕሱን በመግለጽ “ኮፒ” የሚል ምልክት የተደረገበት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣበት በ8ኛው ቀን ማለትም በቀን 20/9/2018 ከቀኑ 9፡40 ገብቶ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰኣት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጲያ የሶዶ ቅ/ ጽ/ቤት በኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ይከፈታል።
6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ ሙሉ መብት አለው።
መ/ቤቱ
Tender details
- Deadline: 2026-05-28
- Bid closing time: 15:40
- Bid opening: 2026-05-28 16:00
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: ካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጲያ በሶዶ ሀገረ ስብከት የኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T11:06:19.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.