የገነተ ኢየሱስ መረዳጃ ዕድር ያስገነባው ሕንጻ የአገልግሎት ቅናሽ /Depreciation cost/ ለማስላት እንዲረዳ የሕንጻው የዋጋ ግምት /Asset Valuation/ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡- ገኢመህ/75/07/2018

የገነተ ኢየሱስ መረዳጃ ዕድር ያስገነባው ሕንጻ የአገልግሎት ቅናሽ /Depreciation cost/ ለማስላት እንዲረዳ የሕንጻው የዋጋ ግምት /Asset Valuation/ ማሠራት ይፈልጋል፤

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታማሉ ባለሙዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኃል።

1. በመንግሥት የንብረት ግምት ፈቃድ ያለው

2. የንግድ ፈቃድ ያለው

3. የብቃት ማረጋገጭ /Certified / የሆነ

4. ለአሴት ቫሌሹኑ ከ5-10 ድርጅቶች በዚህ ሥራ ለመሥራቱ ማረጋገጫ የሚያቀርብ

5. የዘመኑ/የ2018/ግብር የከፈለ

6. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

7. ለአገልግሎቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል

8. ሥራውን አጠናቅቆ የሚያቀርብበትን ጊዜ የሚያቀርብ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ የሚከፍል

ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 /አምሰት ሺ ብር ብቻ/ በአዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 013250560884701 ገቢ ያደርጋል

ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሁድን ሳይጨምር ለ10/ አሥር/ ተከታታይ ቀናት ይቆያል።

ጨረታው የሚከፈተው ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው ባሉበት ወይም ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው ባይገኙም በመረዳጃ ዕድሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተከፍቶ ውጤቱ በማስታወቂያ ይገልጻል።

የዕድሩ ጽ/ቤት ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ከፈረንሳይ ኤምባሲ ከፍ ብሎ የ41 ኢየሱስ ማዞሪያ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ሲሄዱ አዋሽ ባንክ ሥር በሚገኘው ጽ /ቤት ነው።

ለበለጠ መረጃ አቶ መስፍን መሸሻ ስልከ 09 11 66 62 41

አቶ አሰፋ ግርማይ ስልክ 09 12 37 02 36

አቶ ተስፋሁን ከበደ ስልክ 09 11 71 65 01

ዝርዝር የሥራ ተግባራትን በተመለከተ

2. ሕንጻው B +G+ 4 ሆኖ

2.1. ምድር ቤቱ /basement/ ተጠናቅቆ የኪራይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል.

2.2. ወለሉ /Ground/ ተጠናቅቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል

2.3. አንደኛ ፎቅ /first floor/ የንግድ ቤት ተጠናቅቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል

2.4. ሁለተኛ ፎቅ /2nd floor/ አራት መኖሪያ ቤቶች በከፊል የተጠናቀቁና ያልተጠናቀቁ ይገኙበታል

2.5 የቀሩት ሁለት ፎቆች ሦስተኛና አራተኛ ፎቆች በስትራክቸር ደረጃ ያሉ ናቸው

2.6 የሕንጻው ወለል በተለያየ ጊዜ ወደ ኪራይ የገባ ሲሆን የመጀመሪያውን ወለል የተከራየው ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ነው

2.7 የዋጋ ግምቱ ፍትሐዊ በሆነ የአገልግሎት ዋጋና የዓመቱ የዕርጅና ቅናሽ /Depreciation/ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ማመቻቸት.

2.8 ውሉ እንደተጠበቀ ሆኖ ተመሳሳይ ሥራዎችንና ሙያ ነክ የሆኑትን አካትቶ ማቅረብ

2.9 ሥራውን ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ በ20 የሥራ ቀናት ሥራውን አጠናቅቆ የሚያቀርብ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-28
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሁድን ሳይጨምር ለ10/ አሥር/ ተከታታይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-05-28 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የገነተ ኢየሱስ መረዳጃ ዕድር
  • Bid bond: 5,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 17, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T11:55:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders