የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የፓርኪንግ አስተባባሪ፣ የጥበቃ ተራ አስተባባሪ፣ የጽዳት ሰራተኛ እና አትክልተኛ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር: ኢንሥኮ ማዕከል ግዥ /ብግጨ 05/2018

ኮርፖሬሽኑ የፓርኪንግ አስተባባሪ፣ የጥበቃ ተራ አስተባባሪ፣ የጽዳት ሰራተኛ እና አትክልተኛ የውጪ አገልግሎት ግዥ የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የፓርኪንግ አስተባባሪ፣ የጥበቃ ተራ አስተባባሪ፣ የጽዳት ሰራተኛ እና አትክልተኛ ብዛት (በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸ)

1. ተጫራቾች በዘርፉ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታ መክፈቻው ቀን በኋላ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ከግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰአት ከ7፡30 – 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 -6፡30 ድረስ ማመልከቻ በመያዝ ብሎክ 2 አንደኛ ፎቅ ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። (አድራሻው ከስር ተገልጿል።)

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፐሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች ቴክኒክ እና ፋይናንስ ሰነድ በግልጽ ከፋፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናዉ መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

8. ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1(አንድ)

9. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል።

10. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት  ደብረዘይት መንገድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ፖ.ሳ.ቁ. 7858 ስልክ ቁጥር 011 416 7345/ 011 466 9336
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-29
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-05-29 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Trading Businesses Corporation
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T07:23:06.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders