በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን የአግሮ ኬሚካል እና የእንስሳት መድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር የተዘረዘሩትን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የአግሮ ኬሚካል ግዥ
  2. የእንስሳት መድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ግዥ

ከላይ ከተ.ቁ 1(አንድ) እስከ 2(ሁለት) የተዘረዘሩትን ምርቶች ከሀገር ውስጥ ገበያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች በወጣው ማስታወቂያ መሰረት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን በጨረታው ለመሳተፍ፣

1. ከላይ በተዘረዘሩት የንግድ ዘርፎች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት/፣

2. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት

3. የንግድ መለያ ቁጥር TIN ኮፒ፣

4 የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

5 የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ከሚመለከተው ገቢ ሰብሳቢ ተቋም ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

6 ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ : ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::

7 ለመግዛት የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ የያዘ ጨረታ ሰነድ ከዩኒየኑ መግዛት ይቻላል፡፡

8.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 250/ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በዩኒዬኑ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠባሴ ቅርንጫፍ 1000602970713 በመክፈል በደ/ብርሃን ከተማ ጠባሲ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ.የተ.ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡

9.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበትና ለሚሞሉት ዋጋ 2% ሲፒኦ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ በሁለት ፈራሚ የተረጋገጠ በደ/ብረሃን እና አዲስ አበባ ባሉ ባንኮች በዩኒየኑ ስም “ማስያዝ ይኖርባቸዋል ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዶክመንት ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በሁለት ፖስታዎች ተለያይቶ በአንድ ፖስታ ታሽጎ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ. የተ. ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጭምር እስከ 10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጎን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

12. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ ጽ/ ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0927041460 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ የግዥ አይነት የነጠላ ዋጋ እንጂ በሎት(በጥቅል) አለመሆኑን ተረድታችሁ ዋጋችሁን እንድትሰጡ እናሳስባለን፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-28 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: ለአንድ የጨረታ ሰነድ 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር)
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T08:00:30.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders