የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AAC NCB 0010/2018 ዓ/ም

የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የናሙና መለያ

 

የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን

001

በኤሌክትሪክ ወይም በንፋስ የሚነፋ ፍራሽ እና ኮንፈርት ከነትራሱ ግዥ

በተቋሙ ፍላጎት መሰረት

10,000

00

002

የሲሲቲቪ ካሜራ ግዥ

በተቋሙ ስፔስፊኬሽን መሰረት

20,000

00

003

የወንጀል ስፍራ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚያገለግሉ ማቴሪያሎች ግዥ

በተቋሙ ፍላጎት መሰረት

30,000

00

004

የአልባቶች እና ጫማዎች የሙያ ማማከር የአገልግሎት ግዥ (በድጋሚ የወጣ)

በተቋሙ ፍላጎት መሰረት

50,000

00

ስለዚህ፡ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት መቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።

5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከሊራንስ ማቅረብ አለበት።

6. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።

7. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።

9. ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ፣ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።

10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።

11. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።

12. በጨረታ ሰነድ በከፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት።

13. ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀርቡአቸው ዕቃዎች ተቋሙ ባወጣው ፍላጎት መግለጫ/specification መሰረት መሆኑን በተቋሙ የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል።

14. ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር በመከፈል መግዛት ይችላሉ፣

15. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡30 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በተቋሙ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

16, በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ከጠዋት 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል፣

17. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥ፡- 011 862 5800 (011 111 0448)

የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-29 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋት 5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T08:26:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders