የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ እንሰሳት እና አሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት የእንሰሳት ሕክምና መድኃኒቶችና የላብራቶሪ እቃዎች አገልግሎት የሚውል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ደ/ዙ/ገ/ኘ/ግዥ/105/2018

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ እንሰሳት እና አሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት የእንሰሳት ሕክምና መድኃኒቶችና የላብራቶሪ እቃዎች አገልግሎት የሚውል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት፡-

1. በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል

2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር ያላቸው

4. የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አይይዘው ማቅረብ አለባቸው።

7. የጨረታው ሰነድ ከደሴ ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው ከ10/09/2018 ዓ.ም እስከ 24/ 09 /2018 ዓ.ም በአየር ላይ ይውላል።

9. ጨረታው በ25/09/2018 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

10. ተጫራቾች ኦርጅናል መድኃኒት እና የላብራቶሪ እቃዎች መሙላትና ያሸነፉበትን በባለሙያ ማስፈተሽ ማስረከብ አለባቸው።

11. የሚገዙ መድኃኒት እና የላብራቶሪ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

12. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ መድኃኒት እና የላብራቶሪ እቃዎች ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላትና በሎት ስለሆነ በሙሉ መሙላት አለባቸው።

13. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚያቀርቡት መድኃኒት እና የላብራቶሪ እቃዎች ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በጽ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት።

14. ተሸናፊ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ያስያዙት 2% ሲ.ፒ.ኦ ከአምስት ቀን በኋላ ይመለስላቸዋል።

15. አሸናፊው አካል የሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስይዝ ይሆናል።

16. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን መድኃኒት እና የላብራቶሪ እቃዎች በራሱ ወጪ ለሴክተሩ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

17. በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ እስከ 25/09/2018 ዓ.ም ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ እንድያስገቡ እየገለፅን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን።

18. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-7763 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

19. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

20. እያንዳንዳቸዉ መድኃኒት የጊዜ ቆይታ ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።

ማሳሰቢያ፡ አሸናፊው ድርጅት /ተጫራች ኦርጅናል መድኃኒት እና የላብራቶሪ እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል። ስልክ ቁጥር፡- 033 111 7763 ይደውሉ።

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-06-02 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dessie Locality Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T08:28:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders