የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የእርሻ መሣሪያዎች ባሉበት ሁኔታ አንድ ላይ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት በሊዝ ዎርክአውት እና ካፒታል ዕቃ መልሶ መረከብ መመሪያ መሰረት ከአቶ አዱኛ ተስፋ መልሶ የተረከበውን እና ከዚህ በታች የተገለጹትን የእርሻ መሣሪያዎች ባሉበት ሁኔታ አንድ ላይ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የተከራይ ስም
|
በጨረታ የሚሸጠው/ የሚከራየው ንብረት የሚገኝበት ቦታ |
የንብረቱ ዝርዝር ዓይነት
|
የጨረታው መነሻ ዋጋ (በብር)
|
የጨረታው አይነትና ደረጃ
|
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓትና ቦታ
|
|
|
አዱኛ ተስፋ
|
ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ ገላን ክ/ከተማ፣ አትላስ ሪዞርት ወረድ ብሎ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መጋዘን ግቢ ውስጥ፡፡
|
1.Tractor:- (Brand: CASE IH-FARMALL 110JX; Model: TTF 8045.25D.313T; Engine Type: e37;Origin: Turkey year 2022; Condition: Good); Needs Repair & Maintenance- · ብዛት -1 2.Disc Plough:- (Brand: OTOMA; Model:80 O/QD70/E; 4 Discs) . ብዛት 1 |
5,611,588.00
|
ዝግ ጨረታ
|
ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-6፡00 ቦታ፡- በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንጻ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ፤ |
የጨረታው መመሪያ፣
1. ከላይ የተገለጹ ንብረቶችን መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ አካል (ግለሰቦች፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25 በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ እና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ፤ የሚገዙበትን ዋጋ እና የግዢ ሁኔታ በግልጽ በመጥቀስ እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 01 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንጻ 2ኛ ወለል በኢትዮጵያ ልማት ባንከ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቢሮ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፤
2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ ይከፈታል፤
3, የጨረታው አሸናፊ የንብረቱን የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተ.እ.ታ (VAT) ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ ክፍያዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው፤
4. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች፡-
4.1. ቀሪውን ገንዘብ ተ.እ.ታን ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። የጨረታ አሸናፊው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዝው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፤
4.2. ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማቅረብ ወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈለገውን የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ መክፈል ግዴታ አለበት፤
5. ንብረቱን በባንኩ ማሽነሪ ዱቤ ግዢ እና ክራይ መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች፡-
5.1. የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆን፤ እንዲሁም ባንኩ በፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል፤
5.2. በባንኩ አሰራር መሰረት የሚጠበቅበትን ቅድሚያ ክፍያ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመክፈል የባንኩን የማሽነሪ ዱቤ ግዢ እና ኪራይ መስፈርት በማሟላት ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ (CPO) በባንኩ ማህተም ተረጋግጦ ይመለስላቸዋል፤
7. ስለ እያንዳንዱ ንብረት ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንጻ 2ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር +251-11-558- 6175 / 09 11-74-35-02 በስራ ሰዓት ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፤
8. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልግ ከደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መመልከት ይችላሉ፤
9. የጨረታው አሸናፊ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የካፒታል ዕቃውን ለማስተዳደር ማለትም የመጠለያ ኪራይ፣ የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት፤
10.ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-06-04 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 25%
- Published: May 19, 2026
- Posted at: 2026-05-19T08:38:08.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.