በደ/ምዕ/አ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በኡሲቃ ፀበል የሰርቪስ ቤትና የዘበኛ ቤት ግንባታ እና የሸኮ ወረዳ ግብርና አከ/ደ/ጥበቃ ህ/ስራ መጋዘን ግንባታ በግልጽ አወዳድሮ ማስገባት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/አ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በኡሲቃ ፀበል የሰርቪስ ቤትና የዘበኛ ቤት ግንባታ እና የሸኮ ወረዳ ግብርና አከ/ደ/ጥበቃ ህ/ስራ መጋዘን ግንባታ በግልጽ አወዳድሮ ማስገባት ይፈልጋል።
- ሎት 1 በኡሲቃ ፀበል የሰርቪስ ቤትና የዘበኛ ቤት ግንባታ፣
- ሎት 2 የግብርና መጋዘን ግንባታ።
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ድርጅቶች እንዲወዳደሩ ይጋብዛሉ።
1. ደረጃ 5 GC/BC እና ከዛ በላይ የሆኑት
2. ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የስራ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና 12. የዘመኑን የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ።
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑትን የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
5. በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
6. የበጀት ዓመቱ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
7. የጨረታ ማስከበርያ ለሁለቱም ሎቶች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ የሚችሉ።
8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የማወዳደርያ ሰነዳቸውን/ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱ ለብቻ በሰም በማሸግ በመፈረም እና በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ በሸኮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጂናል እና ኮፒ የሚል በግልጽ በሚታይ ቦታ ላይ መፃፍ አለባቸው።
11. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረብያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾችን ህጋዊ ወኪል ፊርማ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።
12. እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበት የስራ ቦታ የተቋራጩ አድራሻ ስልክ ቁጥር ማፃፍ አለበት።
13. ተጫራቾች ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ22ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. አቅራቢዎች የሚሞሉት ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት ካልሆነ መ/ቤቱ የተሞላውን ዋጋ ከነቫቱ እንደተሞላ አድርጎ ነው የሚወስደው።
16. ይህ ጨረታ ለ60/ስልሳ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
አድራሻ፡- ቤንች ሸኮ ዞን ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡- 09 30 57 30 08
በደ/ምዕ/አ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-11
- Publishing entity: Benchi Sheko Zone Sheko Woreda FEDB
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ
- Published: May 18, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.