የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን ግዥ ማለትም፦

1. ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር

2, ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር

3/ ሸልፍ

4. ፕሪንተር

5/ የቢሮ ወንበርና ጠረጴዛ

6/ አልትራ ሞባይል ግዥዎችን ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል።

በግልጽ ጨረታ እቃዎች መግዛት ስለተፈለገ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና ቢሮው ያዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ግልጽ ጨረታ የሚወዳደር አቅራቢ ድርጅት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና በቂ የሆነ የስራ ልምድ ማቅረብ አለበት።

1. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብ ኦርጅናሉ አንድ ፖስታ ሁለት ኮፒዎቹን ኮፒ አንድ እና ኮፒ ሁለት በተናጠል በፖስታ በማሸግ የተጫራቾች ስምና ፊርማ በግልጽ ተጽፎባቸው ሶስቱም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጐ በሠም በኤንቨሎፕ ታሽጐ መቅረብ ሲኖርበት የተለያዩ የቢሮ እቃዎቹን ግዥ ለሚጫረቱ እቃዎች ግዥ ዓይነቱና መጠኑ ስእላዊ መግለጫ የሚያስፈልገው ስለሆነ በከለር የታተመ ስእላዊ መግለጫ በፖስታ ውስጥ ተደርጐ በተወሰነ ጊዜና ሠዓት በአፋር ብ/ክ/መንግስት ከተማ ልማት ኮንስትራከሽን ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሂሳብ ቢሮው ለመግዛት የፈለገውን የተለያዩ የቢሮው እቃዎችን ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት መጫረቻ ሰነድ ግልጽ አድርጎ በመሙላት እያንዳንዳቸው 1/ አንድ/ ኦርጅናልና 2/ኮፒ/ ሰነድ ማምጣት ግዴታ አለባቸው።

3. የሚገዙ የቢሮ እቃዎችን ዝርዝር መግለጫ/specification/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

4. ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ ለሚያቀርባቸው እቃዎች ዋጋ 1 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ቼክ ወይም/CPO/ ከመወዳደሪያ ሂሳብ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ ታሽጐ በሰም ኤንቨሎኘ ማቅረብ አለበት።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ ከፍለው ከከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይችላሉ።

6. የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዶክመንት ሽያጭ የሚደረግ ሲሆን 16ኛ ቀን እስከ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ተጫራቾች ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ/ብ/ክ/መንግስት በከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/ አስ/ዳይሮክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል። ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጨረታው የሚገባና የሚከፈት ይሆናል።

7. ሻጭ ንብረቱን ንብረት ክፍል ድረስ ወስዶ ካስረከበ በኋላ በስሙ ሞዴል 19 አስቆርጦ ሂሳብ ክፍል ወስዶ ሂሳቡን ማወራረድ አለበት።

8. የጨረታ መክፈቻ ኘሮግራሙን ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ቢቀሩ የጨረታው መክፈት ሂደት አይስተጓጉልም።

9. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎት በስልክ ቁጥር 033-666-0003 /05 እና

በኢሜል afarudcb@gmail.com ደውለው ይጠይቁ።

የአፋር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዶክመንት ሽያጭ የሚደረግ ሲሆን 16ኛ ቀን እስከ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-02 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዶክመንት ሽያጭ የሚደረግ ሲሆን 16ኛ ቀን እስከ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Afar City Development Construction office
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T11:10:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders