በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት ግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም የግብርና ኖራ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ለማጓጓዝ የጭነት ማመላለሻ መኪናዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት ግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም የግብርና ኖራ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ለማጓጓዝ የጭነት ማመላለሻ መኪናዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት የትራንስፖርት አገልግሎት ለማቅረብ የሚፈለጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።

2. የዘመኑን የቴክኒክ ምርመራ አልፎ ቦሎ ያለው::

3. የተሟላ የመድን ሽፋን ዋስትና ያለው::

4. የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ::

5. የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያመለክት የጨረታ ሰነድ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ ግብርና ቢሮ ስም በተከፈተ አካውንት ቁጥር 1000454620918 ገቢ በማድረግና አድቫይስ በመያዝ ከደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ ግብርና ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ ግብርና ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቁጥር 04 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ታሽጎ በ31ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ ግብርና ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር  ዳይሬክቶሬት ቁጥር 04 ይከፈታል።

9. የጨረታ መዝጊያ ወይም መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቀን ይሆናል።

10. የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።

11. መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- ስልክ ቁጥር 047 331 2048/ 047 331 2145
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Publishing entity: የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ /ቦንጋ/
  • Bid bond: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 19, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders