Amharic

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የዕንቁላል ጣይ ዶሮ ቤት በሴቶች ለተደራጁ ማህበራት የአንድ ቀን ጫጩት ማሳደጊያ ቤት ግንባታ ለማካሄድ በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል

Description

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 438

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ በ(SVCD SP) ፕሮጀክት በጌዴኦ ዞን በ2 ሎት በመከፋፈል በሎት 1 በይርጋ ጨፌ ወረዳ ሀሩ ከተማ እና በሎት 2 በኮቾሬ ወረዳ ቡኖ ከተማ የዕንቁላል ጣይ ዶሮ ቤት በሴቶች ለተደራጁ ማህበራት የአንድ ቀን ጫጩት ማሳደጊያ ቤት ግንባታ ለማካሄድ በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት

1. G C 6 /B C 5 እና ከዚያ በላይ

2. በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡና በ2018 ዓ.ም የንግድ ሥራ ፈቃድ ያሳደሱ

3. ከመንግሥት የሚፈለግበት የግብር እና የታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ ለበጀት ዓመቱ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ደብዳቤ ከታክስ አስተዳደር ቢሮ እና አቻ ተቋም ማቅረብ የሚችል

4. ወርሃዊ የታክስ ማስታወቂያ በማቅረብ የሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከሚመለከታቸው ገቢዎች ጽ/ቤት የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል

የግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸውና ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ እና ውል ያላቋረጡ ተቋራጮችን እየጋበዘ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተቋራጮች የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር / በፕሮጀክቱ ስም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ገቢ በማድረግና ደረሰኝ በመውሰድ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናል ይዘው በመቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶቻቸውን በመሙላት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ አድርጎ በኤንቨሎፕ በማሸግ በእያንዳንዱ ላይ ማህተሙንና ፊርማውን በማሳረፍ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ ሰነድ እያንዳንዱን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

በኦርጅናል ሰነድ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መልክ በድጋሚ መጻፍ ይኖርበታል። እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 70,000 (ሰባ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለ 90 ቀን ማቅረብ ይኖርበታል።

በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጪ ያደርጋል።

ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ የሚዘጋው በ31ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ክፍሎች በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡3ዐ ሰዓት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት ይሆናል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር ---በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟላ የሚቀርብ የሥራ ተቋራጭ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።

አንድ ተጫራች ከ1 ሎት 1 በላይ መወዳደር አይችልም።

የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የማብራሪያ ግድፈት ካለው የጨረታ ዶክመንት (Bid Document) 1TB የበላይነት ይኖረዋል።

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ31ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-18 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ31ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: South Ethiopia's Regional State Agriculture Bureau
  • Bid bond: 70,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (May 19, 2026)
  • Posted at: 2026-05-19T12:41:13.000Z
← Back to all tenders