ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ጎዴ፣ ጋሸና፣ አዲግራት፣ አጣዬ፣ መካነሰላም እና ደላንታ መስመር የዳሽን ቢራ ምርቶችን ለማከፋፈል መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ጎዴ ፣ጋሸና ፣ አዲግራት፣ አጣዬ፣ መካነሰላም እና ደላንታ መስመር የዳሽን ቢራ ምርቶችን ለማከፋፈል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
2. በቂ ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚችል (የራሱ ቢሆን ይመረጣል)
3. ምርቱን ለማከማቸት የሚሆን መጋዘን (የራሱ ቢሆን ይመረጣል)
4. በዘርፉ ተዛማጅ የስራ ልምድ ያለው
5. የስራ ማስኬጃ በቂ ካፒታል ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ነዋሪ የሆነና በአካባቢው ማህበረሰብ መልካም ስም ያላቸው፤
6. ማህበራዊ እና ህጋዊ ግዴታዎችን በአግባቡ እየተወጣ ያለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
7. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን ሠነድ አሟልተው አዲስ አበባ፣ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ዋና መስሪያ ቤት (22 የቱሪስት ንግድ ስራ ድርጅት አጠገብ) ከሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 1000 (አንድ ሺ ብር) ገዝቶ በመሙላት ጨረታውን መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን::
8. ጨረታው ከግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 27 2018 ዓ.ም ድረስ አየር ላይ የሚቆይ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
9. ጨረታው ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ/ም ጠዋት 4:00 ተዘግቶ በዚያው እለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀጣይ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
10. ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-04 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Dashen Breweries S.C.
- Buyer TIN: 0001447387
- Bid document price: 1000.00 ብር
- Published: May 19, 2026
- Posted at: 2026-05-19T14:23:26.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.