ዋን ኤከር ፈንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የዋንዛ ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

★ Featured

Description

የዋንዛ ዛፍ ዘር የዋጋ ማቅረቢያ ጥያቄ (Request for Quotation - RFQ)

ዋን ኤከር ፈንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የዋንዛ ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ይህንን ዘር ችግኞችን ለማፍላት ጥቅም ላይ የሚዉል ሲሆን፣ ችግኞችን ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል (በማሰራጨት)፣ አርሶ አደሮቹ ዛፎችን በማልማት ሀብታቸውን እንዲጨምሩ፣ ገቢያቸውን እንዲያሰፉ እና አካባቢያቸውን እንዲያለሙ (እንዲያሻሽሉ) ይደረጋል።

● የሚያስፈልገው የዋንዛ ዘር መጠን 8,100,604 ዘሮች ነው ይህም በአንድ ኪሎ ግራም 3,500 ዘሮች እንዳሉ በመገመት 2,600 ኪሎ ግራም ዋንዛ ዘር ይፈለጋል። ይህ መጠን ውል ከመፈረሙ በፊት ሊቀየር ይችላል

● ተጫራቹ የዋንዛ ዘሩን በራሱ ወጪ ማጽዳት/ማሳጠብ አለበት።

● እኛ የምንመርጠው ንጹህ፣ ቀለማቸው ፈካ ያለ ቡናማ ፣ ያልተሸበሸቡ፣ እና ቀዳዳ ወይም ጉዳት የሌለባቸውን ዘሮች ነው ።

● (OAF) ከተጫራቹ መጋዘን የተመረጠ ዘር ናሙና ይፈልጋል። ይህ ናሙና በተሻለ ሁኔታ በOAF ሰራተኞች ይሰበሰባል (በጸጥታ ምክንያት የኦአኤፍ ሰራተኞች የተጫራቹን መጋዘን በወቅቱ ለመጎብኘት አስቸጋሪ ካልሆነ በስተቀር)፤ በተጫራቹ የተላኩ ናሙናዎች ዝቅተኛ ነጥብ ያገኛሉ።

● ዘሩ በ2026 የምርት ዘመን የተሰበሰበ መሆን አለበት።

● ተጫራቾች በኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት የሚያስችላቸውን ተገቢ እና ህጋዊ ፍቃድ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።

● ተጫራቾች ሁሉም ክፍያዎች ከተፈጸሙ በኋላ ህጋዊ ደረሰኝ ለ ዋን ኤከር ፈንድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

● አቅራቢው ዘሩ በክልላቸው የኳራንቲን ፅህፈት ቤት እንዲረጋገጥ ፈቃደኛ መሆን አለበት።

● ሁሉም ጨረታዎች ከገቡ በኋላ፣ አቅራቢዎች ዋጋቸውን በድጋሚ አሻሽሎ ለማቅረብ አንድ እድል ይሰጣቸዋል።

● ዕጩ የተደረጉ (Shortlisted) አቅራቢዎች የOAF የብቅለት ምርመራ (germination test) እስኪጠናቀቅ ድረስ ለመጠበቅ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፣ ይህም እስከ 6 ሳምንታት ሊወስድ ይችላል።

ለመጫረት የምትፈልጉ ህጋዊ የዘር አቅራቢዎች የሚከተለውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት፣ በመፈረም እና ማህተም በማድረግ በሚከተለው አድራሻ በኩል ይላኩ፦

● በኢሜል፦ ethiopia.bidsubmissions@oneacrefund.org

ማሳሰቢያ፡ ማንኛውንም የዋን አከር ፈንድ ሰራተኛ ጉቦ ለመስጠት መሞከር ከድርጅቱ ጋር እስከመጨረሻው መታገድን ያስከትላል ።

የጨረታው ማብቂያ ቀን June 3, 2026

ጥያቄ

መልስ

የአንድ ኪሎ ግራም የተጣራ የዋንዛ ዘር ዋጋ?

 

ዘሮቹ መቼ ነው የተሰበሰበው?

 

ዘሮቹ ከየት አካባቢ ነው የተሰበሰበው?

 

ናሙናው የሚሰበሰብበት የእርስዎ መጋዘን የት ነው የሚገኘው?

 

የOAF ሰራተኞች ከመጋዘንዎ ናሙና እንዲወስዱ ፍቃደኛ ነዎት?

 

ናሙና ከተሰበሰበ በኋላ OAF የውስጥ ናሙና ምርመራውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ (እስከ 6 ሳምንታት ሊወስድ ይችላል) ለመጠበቅ ፈቃደኛ ነዎት?

 

የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የቲን (TIN) ሰርተፍኬት አለዎት?

 

በአማራ ክልል ላለ ድርጅት ለመሸጥ ህጋዊ ፍቃድ አለዎት?

 

ለ OAF ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይችላሉ?

 

● ዋን ኤከር ፈንድ በማንኛውም ምክንያት ማንኛውንም አቅራቢ የመቀበል ወይም ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

● ዋን ኤከር ፈንድ ከማንኛውም አቅራቢ ያገኘውን ምርጥ ዋጋ ለሁሉም ተጫራቾች የማጋራት መብት አለው ።

● ዋን ኤከር ፈንድ ውል ከመፈረሙ በፊት በማንኛውም ጊዜ ይህንን ጨረታ ሙሉ በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል ።

●ዋን ኤከር ፈንድ ለተለያዩ አቅራቢዎች የተለያየ መጠን ሊመድብ ይችላል ። እንዲሁም የተሰጠውን መጠን ከመግዛት ሊቆጠብ ይችላል ። መጠኖቹ የመጨረሻ አይደሉም፣ እና የመጨረሻ ውል ከመፈረሙ በፊት ሊቀየሩ ይችላሉ ።

● ዋን ኤከር ፈንድ ጨረታውን ወይም የጨረታውን ማንኛውንም ገጽታ የማሻሻል እና በማንኛውም አቅራቢ የቀረበውን ጨረታ በማንኛውም ምክንያት፥ ለዚያ ውሳኔ እና እርምጃ ምክንያት ማቅረብ ሳያስፈልገው ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ስም-------------------------               ፊርማ----------------------------        ቀን----------------------------------


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-06-03 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: One Acre Fund
  • Buyer TIN: 0041750397
  • Buyer address: Yeka Sub City, Woreda 8, Level 5, Building Opposite Misrak Polytechnic College, Addis Ababa, Ethiopia Or Kebele 13, Bahir Dar, Amhara Region(Bahir Dar office)
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T07:02:06.000Z
  • Buyer website: https://oneacrefund.org/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders