በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የተለያዩ ግንባታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለስልጤ ኤፍ ኤምና ቴሌቪዥን ጣቢያ የቴሌቪዥን ስቲዲዮ ግንባታ እና ለስልጤ ዞን አስተዳደር እንግዳ ማረፊያ የመፀደጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ደረጃቸው B.C/G.C-6 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤
- ሎት 1. የቴሌቪዥን ስቱዲዮ ግንባታ
- ሎት 2. የመጸደጃ ቤት ግንባታ
የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፤
የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፤ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤ ለሎት 1 እና ለሎት 2 ለየብቻ ለያንዳንዳቸው የጨረታ ዋስትና 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፤
የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሎት 1 እና ሎት 2 እያንዳንዱን ሰነድ ለየብቻ ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ ብር 800/ስምንት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በ20ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 20ኛው ቀን የስራ ቀን ከልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፦
ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ። የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጡም።
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 046 771 0586 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በማዕ/ኢ/ክ/መ/ የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-08
- Publishing entity: Silte Zone Finance Department
- Bid bond: 40,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 800.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: May 20, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.