የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የምግብ ጥሬ እህል፣ አጥንት የሌለው የበሬ ሥጋ፣ ማጣፈጫዎችን፣ ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችን እና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ከሀምሌ 01/11/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/01/2020 ዓ.ም ድረስ 15ወራቶች የሚቆይ ለሕግ ታራሚዎች የምግብ ጥሬ እህል፤ አጥንት የሌለው የበሬ ሥጋ ፤ ማጣፈጫዎችን ፤ ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችን እና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ ሰርተፍኬትና ቲን ነምበር / Tin Number / ያለው የዘመኑን ንግድ ግብር አጠናቆ የከፈለ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 / ሃምሣ ሺህ ብር ብቻ / በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ያለፈ እያንዳንዱ ሰው ባለፈው ልክ የውል ማስከበሪያ ብር 300.000.00/ ሦስት መቶ ሺህ ብር ብቻ ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝና በጨረታው ደንብ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ሁሉ ማሟላት የሚችል ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባለው 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር ብቻ / በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ቢሮ ቁጥር 08 ቀርቦ በመግዛት በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የምግብ ጥሬ እህል፤ ማጣፈጫና የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦችን በዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በመሙላት በታሸገ ኤምበሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው የምግብ ጥሬ እህል፤ ማጣፈጫዎችንና ልዩ ልዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦችን ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በጋዜጣው ላይ በተጠቀሰው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3:30 /ሶስት ሰዓት ተኩል/ ላይ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው / በተገኙበት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ታሽጎ በእለቱ ከጧቱ 4:00 ሰዓት ላይ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ውስጥ የሚከፈት መሆኑንም ጭምር እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ ፡

  • ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  • ተጫራቾች የሁሉ ዕቃ ዓይነት ዋጋ መሙላትና ዋጋቸውን አባዝተው የማስቀመጥ ግዴታ አለባቸው፤
  • የጨረታ አሸናፊ በጨረታ ያሸነፋቸውን ዕቃ በራሱ ትራናስፖርት ወደ ተቋሙ ማድረስ አለበት።
  • በተጨማሪ ናሙና የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው መሆኑን እያሳወቅን ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን።
  • ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 776 0126/ 046 776 0125 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም


Tender details

  • Deadline: 2026-06-06
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3:30
  • Bid opening: 2026-06-06 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4:00
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Chencha Correctional Facility
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሣ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T08:00:17.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders