የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ለህጻናት ማቆያ የሚያገለግሉ የዴይ ኬር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- ኢፕድ 021/2018
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ለህጻናት ማቆያ የሚያገለግሉ የዴይ ኬር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል መሆኑና ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው።
4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1ኛ ፎቅ በአቅርቦት መምሪያ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0111569869
ኢሜይል procurement@press.et
አድራሻ ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-06-04 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T08:37:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.