የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎች በድርድር ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል
Description
የድርድር ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ለአቶ ምእራፍ ተገኘ አለሙ በሊዝ ፋይናንሲንግ ስርዓት ለግብርና ሜካናይዜሽን ፕሮጀክት አገልግሎት ዘርፍ አከራይቶ የነበራቸውን የእርሻ መሳሪያዎች ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በገቡት የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውል መሰረት ሊከፍሉ ባለመቻላቸው ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/98 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 807/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት መልሶ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል።
|
የተከራይ ሙሉ ስም |
በጨረታ የሚሸጠዉ(የሚከራየው) ንብረት ሁኔታ |
የድርድር ሸያጭ የሚካሄድበት |
|||
|
ዓይነት |
አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ |
ቀን |
ቦታ |
|
|
አቶ ምእራፍ ተገኘ አለሙ
|
ማሲ ፈርጉሰን ትራክተር 132 የፈረሰ ጉልበት ያለው በዛት 01 |
ሰቲት ሁመራ ዞን ሁመራ ከተማ የባንኩሁመራ ቅርንጫፍ
|
14,221,463.69
|
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም
|
የኢትዩጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ጽ/ቤት
|
|
ማረሻ ናርዲ ባለ 5 (አምስት )ዲስክ ብዛት 01 |
|||||
|
መከስከሻ ባልዳን ባለ 24 (ሃያ አራት) ዲስክ ብዛት 01 |
|||||
የሽያጩ መመሪያ፡-
1. ከላይ የተመለከቱትን ንብረቶች በጥሬ ገንዘብ መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰቦች፡ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የንብረቱን የሚገዛበትን ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ)በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በተዘጋጀና በባንክ በተረጋጋጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ዲስትሪክቱ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መደራደር ይቻላል።
2. የሐራጁ አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ተመሳሳይ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠበቁ ማናቸውንም ቀረጥና ሌሎች ክፍያዎች በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት።
3. አሸናፊው በተደራደሩበት/ባቀረቡት የድርድር ዋጋ ላይ 15% VAT/ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለባቸው።
4. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ዋጋ ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ካልከፈለ ባንኩ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ተደርጎ ሽያጩ በድጋሚ ይካሄዳል ።
5. ላላሸነፉ ተደራዳሪዎች ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
6. አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ ቢያንስ የማሽኑን ጠቅላላ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) በቅድሚያ በመክፈል በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟለት የማሽነሪ ኪራይ የዱቤ ግዥ ውል መፈረም ይኖርበታል ። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
7. ንብረቶችን ከጨረታ ቀን በፊት ማየት ወይም መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ ከባንኩ ጋር ፕሮግራም መያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ለማንኛውም ማብራሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም
በስልክ ቁጥር
0582210221/ 0582110184 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-06-09
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም
- Bid opening: 2026-06-09 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም
- Region: Amhara
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 20%
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T08:44:46.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.