የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአርባ ምንጭ ኤርፖርት (አውሮፕላን ማረፊያ) የደህንነት አጥር ግንባታ ሥራ የሚያከናውኑ ደረጃ ሶስት (3) ጠቅላላ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: - SSNT_T616
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአርባ ምንጭ ኤርፖርት (አውሮፕላን ማረፊያ) የደህንነት አጥር ግንባታ ሥራ የሚያከናውኑ ደረጃ ስሶት (3) ጠቅላላ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ፕሮጀክቱን የማጠናቀቂያ ጊዜ ስራው ከተጀመረበት በ180 ቀናት ውስጥ ይሆናል፣
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
1. ተጫራቹ ለ2018 ዓ. ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት (TIN) ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላል፡፡
2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ ሶስት ጠቅላላ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጭ የሆነ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
3. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
4. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (ብር 200.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT_T616 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (Scan Copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional and Irrevocable Bank Guarantee) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጋር ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ቴክኒካል የጨረታ መክፈቻ ክፍል በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
አቶ ልመንህ ጋሻው
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-8953
ኢ-ሜይል: LimenihG@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-06-04 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Buyer TIN: 0000028498
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T08:46:10.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.