የሜታ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ አቃዎች እና ኢኒስታሌሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር W/M/A/META-2018-003

የሜታ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የወረዳው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ አቃዎች እና ኢኒስታለሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ዕቃዎቹን ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ/ያደሰ መሆን አለበት።

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።

4. የጨረታው ማስከበሪያ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በሜታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሠርቶ ማቅረብ የሚቸል።

5. ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስና ወንጀል እና ኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን አለባቸው::

6. የጨረታው አሸናፊ ያሽነፈቸው ዕቃዎች በተባለበት ቦታ ማድረስ የሚችልና ያሽነፋቸው ዕቃዎች በሚፈለገው መጠን ያለው መሆን አለበት።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሽህ ብር) በመክፈል በምስ/ሐ/ መስ/የሜታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውና ኮፒ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16 ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች እና ሀጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

10. እቃዎች በኢትዮጵያ ማቴሪያል እስታንዳርድ የተረጋገጠ መሆን እንዳለበት ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው፡በዚህ ያልተረጋገጠ እቃ ካላቀረቡ መ/ቤቱ እንደማይቀበል ማወቅ አለባቸው።

11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913 364 555 /0913 393 596 በስራ ስአት ደዉለው ወይም በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
በምስራቅ ሐረርጌ መስተዳድር የሜታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-06
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-06 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በምስራቅ ሐረርጌ መስተዳድር የሜታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር)
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T08:51:14.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders