በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የኮምቦልቻ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኢኒስታሌሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር WMAK-BMA‐2018-002

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የኮምቦልቻ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የወረዳው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች እና ኢኒስታለሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ዕቃዎቹን ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ/ያደለ መሆን አለበት።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
  4. የጨረታው ማስከበሪያ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚቸል።
  5. ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስና ወንጀል እና ኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን አለባቸው።
  6. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በተባለበት ቦታ ማድረስ የሚችልና ያሸንፋቸው ዕቃዎች በሚፈለገው መጠን ያለው መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በምሥሐ መስ/የኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
  10. እቃዎች በኢትዮጵያ ማቴሪያል እስታንዳርድ የተረጋገጠ መሆን እንዳለበት ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው። በዚህ ያልተረጋገጠ እቃ ካቀረቡ መ/ቤቱ እንደማይቀበል ማወቅ አለባቸው።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 15 76 68 40 / 09 15 04 29 15 በስራ ሰዓት ደውለው ወይም በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ።

በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-06
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-06 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የኮምቦልቻ ወረዳ የገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Bid bond: 500,000 ብር
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T09:05:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders