በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አጀንዳ፣ የጠረጴዛ ካላንደር እና የእንኳን አደረሳችሁ ካርድ በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ቁጥር ሙሊፋ 43/2018 ዓ.ም
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ አጀንዳ፣ የጠረጴዛ ካላንደር እና የእንኳን አደረሳችሁ ካርድ በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ (2018ዓ.ም) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ሰነድ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከነቫቱ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት (ገርጂ የዱሮ ኢምፔሪያል ሆቴል ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቀድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በዕለቱ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብረካ
ስልክ 011 442 0216
ፋክስ 011 442 0688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሸን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-06-02 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Mugher Cement Factory
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር)
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T09:06:32.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.