Promotional items and merchandise

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ማህበራት ህብረት (ሲሲአርዲኤ)/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ለማህበረሰብ በጎ ፈቃደኞች የሚውሉ 6,700 የካንቫስ ቦርሳዎችን ለማምረትና ለማቅረብ ብቃትና ልምድ ያላቸውን አቅራቢዎች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የካንቫስ ቦርሳ ግዥ

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ማህበራት ህብረት (ሲሲአርዲኤ)/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ለማህበረሰብ በጎ ፈቃደኞች የሚውሉ 6,700 የካንቫስ ቦርሳዎችን ለማምረትና ለማቅረብ ብቃትና ልምድ ያላቸውን አቅራቢዎች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. የግዥው ዝርዝር

  • የዕቃው ዓይነት፡ የካንቫስ ቦርሳ (Canvas Bag)
  • ብዛት፡ 6,700
  • በቦርሳው ላይ ሲሲአርዲኤ/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት እና የአጋር ድርጅቶች አርማዎች እንዲሁም ከበጎ ፈቃደኝነትና ከፕሮግራሙ ጋር የተያያዘ መልዕክት ጥራት ባለው ቋሚ ቀለም መታተም አለበት።
  • ዝርዝር ቴክኒካል መመዘኛ (Specification) በጨረታ ሰነዱ መሠረት ይሆናል።

2. ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገቡ መስፈርቶች

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
  • የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (TIN/VAT እንደአግባቡ)፤
  • ተመሳሳይ ሥራ የማከናወን ልምድ ያለው መሆኑን የሚገልጥ ማስረጃ፤
  • የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛል ማቅረብ፤
  • የተጠናቀቀ የቦርሳ ናሙና (Sample) ማቅረብ።

3. የማስረከቢያ ጊዜ

አሸናፊው ተጫራች ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ 25 ቀናት ውስጥ ሙሉ ትዕዛዙን አጠናቆ ማስረከብ አለበት።

4. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ

  • ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ (ToR) ከሲሲአርዲኤ መ/ቤት በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበቅ ቀን ጀምሮ ቢሮ ቁጥር 304 በመገኘት መውሰድና መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የቴክኒክ ፕሮፖዛል፣ የፋይናንስ ፕሮፖዛል፣ የሥራ ዕቅድ እና የተጠናቀቀ ናሙና በታሽገ ፖስታ ለሲሲአርዲኤ/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ቢሮ፣ ቢሮ ቁጥር 304 እስከ ማክሰኞ ነሐሴ 12 ቀን 2026 እስከ 10፡30 ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

5. ማሳሰቢያ

  • የአርማዎች ፋይልና የህትመት መልዕክት በሲሲአርዲኤ/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ይቀርባል። የቀረበው ናሙና ከተፈቀደ በኋላ የብዛት ምርት ይጀምራል።
  • (ሲሲአርዲኤ)/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ጨረታዎች የመቀበል ወይም ያለምንም ምክንያት የመሰረዝ መብት አለው።

ለበለጠ መረጃ - 09 11 42 78 91/009 11 64 39 37

አድራሻ፡ የክርስቲያን በጎ አድርጎት እና ልማት ማኅበራትህብረት (CCRDA)፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ደብረ ዘይት መንገድ፣ ከአሽከርካሪዎችና መካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት።


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid opening: 2026-08-18 16:30
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Consortium of Christian Relief and Development Association (CCRDA)
  • Buyer address: Akaki kality Sub City, Debreziet Road In front of Drivers and Mechanics Training Centre
  • Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T13:30:30.000Z
← Back to all tenders