ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጎማን መልሶ መጠቀም ቴክኖሎጂን ሥራ ላይ በማዋል ጎማዎችን በመፍጨት እና የተለያዩ ግብዓቶችን በመጠቀም ለሕፃናት መጫዎቻ፣ ለጂም ቤቶች፣ ለእግረኛ መንገድና ለተለያዩ ስፖርታዊና የመዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የራበር ምርቶችን ማለትም Rubber Tiles (Dog Bone), Interlock Playground እና Flat Playground (Standard

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጎማን መልሶ መጠቀም ቴክኖሎጂን ሥራ ላይ በማዋስ ጎማዎችን በመፍጨት እና የተለያዩ ግብዓቶችን በመጠቀም ለሕፃናት መጫዎቻ፣ ለጂም ቤቶች፣ ለእግረኛ መንገድና ለተለያዩ ስፖርታዊና የመዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የራበር ምርቶችን ማለትም Rubber Tiles (Dog Bone), Interlock Playground እና Flat Playground (Standard Rubber Tile) በተለያየ ቀለም ዓይነቶች በከፍተኛ ጥራትና የአገልግሎት ዘመን እያመረተ የሚገኝ ሲሆን፣ ምርቶቹን ለአከፋፋዮች በጨረታ አወዳድሮ የአንድ ዓመት ውል በመፈራረም ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስስሆነም ተጫራች ከዚህ በታች የተመስከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ አግባብነት ያለው እና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በተለምዶ ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግሩ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዋና መ/ቤት GlW ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አሥር ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ከታች የጨረታ መዝጊያ ተብሎ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከታች የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በግል ማህበሩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
  6. የግል ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የጨረታው መዝጊያ ቀን፡- ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሠዓት

ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

ዋና መ/ቤት GlW ህንፃ 2ኛ ፎቅ

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ +251 91 783 2984 / 251 91 061 4251


Tender details

  • Deadline: 2026-05-30
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-05-30 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ECOSCO RISING HONGOFA Plc
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T10:47:03.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders