ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሰፊ እና አረንጓዴ ግቢያችን የተሳካ የልጆች የክረምት ፕሮግራም (Summer Camp) ያካሄድን ሲሆን በመጪው 2018 ዓ.ም. የክረምት ወራትም በዘርፉ ልምድ ካላቸው ተቋማት ወይም ግለሰቦች ጋር በጋራ ለማዘጋጀት እንፈልጋለን

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፈቃድ አግኝቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ አካባቢ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያ የትምህርት ዘርፎች ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ የትምህርት ተቋም ነው።

በመሆኑም ያለበትን የማህበረሰብ አገልግሎት ለመወጣት ባለፉት ዓመታት በተመቻቸዉ ሰፊ እና አረንጓዴ ግቢያችን የተሳካ የልጆች የክረምት ፕሮግራም (Summer Camp) ያካሄድን ሲሆን በመጪው 2018 ዓ.ም. የክረምት ወራትም በዘርፉ ልምድ ካላቸው ተቋማት ወይም ግለሰቦች ጋር በጋራ ለማዘጋጀት እንፈልጋለን። ስለሆነም የክረምት ፕሮግራም (Summer Camp) በማዘጋጀት ልምድ ያላችሁ ተቋማት ወይም ግለሰቦች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ጀሞ 1 ለቡ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር C-116 በአካል መጥታችሁ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን አናሳውቃለን።

ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 74 17 66 00 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደምትችሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ
  • Bid opening: 2026-05-30 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hope Enterprise University College
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T11:40:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders