የአ/ቃ/ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ለሴክተሮች የሚያስፈልጉ የአገልግሎት ግዥዎች /የህትመት ሥራዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች እና የዋንጫዎች/ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
የአ/ቃ/ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ለሴክተሮች የሚያስፈልጉ የአገልግሎት ግዥዎች /የህትመት ሥራዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች እና የዋንጫዎች/ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- የህትመት ሥራዎች፤
- ሎት 2፡- የመኪና ኪራይ፤
- ሎት 3፡- የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች፤
- ሎት 4፡ የዋንጫዎች ግዥ፤
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
2. የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ያለው
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
4. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
5. የጨረታ ማስከበሪያ CPO
- ሎት፡-1- 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/
- ሎት 2፡- 45,000.00 /አርባ አምስት ሺህ ብር ብቻ/
- ሎት 3፡- 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር ብቻ/
- ሎት 4፡ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ ሲፒኦ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ያሰራሉ።
ተጫራቾች የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ለሚወዳደሩ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ብቻ የተሳተፉ እና ካደራጃቸው አካል ስድስት ወር ያልሞላው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
6. የአሸናፊው ድርጅት CPO ተመላሽ የሚሆነው የውል ማስከበሪያ የአጠቃላይ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% ሲያሲዝ ብቻ ነው።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከመስሪያ ቤቱ በገዙት ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ በግልጽ እና በሚታይ መልኩ ያለ ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን በተለያ የፖስታ በማሸግ ሁለት ፖስታ በአንድ ላይ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) የሥራ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
8. በአስራ አንደኛው (11) የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ተጫራጮች ሰነድ በማስገባት 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ልክ 4፡30 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሁለተኛ ፎቅ ጨረታው ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ፡- አድራሻ ከቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደር ህንፃ ላይ ሁለተኛ ፎቅ መጠየቅ ይችላሉ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-30
- Publishing entity: Akaki Kality Sub City Design Construction Works Pool Government Procurement Administration
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 18, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.