ኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አክሲዮን ማኅበር አንድ (1) FORD E 350 ሞዴል በጥሩ አቋም ላይ ያለ ፎርድ አምቡላንስ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አክሲዮን ማኅበር አንድ (1) FORD E-350 ሞዴል በጥሩ አቋም ላይ ያለ ፎርድ አምቡላንስ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተሽከርካሪው የተሠራበት ዘመን እ.ኤ.አ 2009፤ በናፍጣ የሚሠራ የሞተር ፈረስ ጉልበት 184፤ የሞተር 6000 ሲሲ ' ስምንት ስሊንደር እና አንድ አክስል ነው።

1. የጨረታ ሰነዶች፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አ.ማ. ፋይናንስ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሠባት (7) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጧቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ እንድሁም ቅዳሜ ከጧቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

2. የብቃት መስፈርት፡ 

2.1.የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ሠርቲፍኬት ከግብር ከፋይ መለያ ሠርቲፍኬት ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

2.2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አ.ማ. ስም ጨረታው ፀንቶ ለሚቆይባቸው ለተጨማሪ 28 (ሃያ ስምንት) ቀናትን የሚሸፍን ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታ መክፈቻ፤ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት በ8ኛው (ስምንተኛው) ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማኀበሩ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ባለው የመሰብሰቢያ አደራሽ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።

4. ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 667 8646 ወይም 011 667 8552 መደወል ይቻላል።

5. አክሲዮን ማኅበሩ ሌላ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፣ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻችን፡ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 3፣ የቤት ቁጥር አዲስ፡ ፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ወደ አቤም ሆቴል መሄጃ መንገድ ላይ አይ ሲ ኤም ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-26
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሠባት (7) ተከታታይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-05-27 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ8ኛው (ስምንተኛው) ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: International Cardiovascular Medical Center Share Company
  • Buyer TIN: 0001228470
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T11:55:01.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders