የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (Electric Vehicle) መግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ERC DSPA ግ.ጨ.ቁ 14/2018
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አቅርቦቶች ፍላጎት ካላቸው የአገር ውስጥ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
1. የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ( Electric Vehicle) ግዢ
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት አለበት፡-
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ
- በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን/
- ታክስ ክሊራንስ
- ተጫራቾች በሽርክና በጥምረት በጋራ ወይም በቅንጅት የሚጫረቱ ከሆነ የመመስረቻ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፤
- ርክክቡ የሚፈጸምበት ቦታ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋናው መስራያ ቤት ነው፤
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ 30 (ሰላሳ) ቀናት
- የጨረታ ማስከበሪያ መጠን
ሎት 1 (Light Electric Vehicle 1) 120,000.00 / መቶ ሀያ ሺ/ ብር ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው በሲ.ፒ.ኦ ፤ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሆኖ ጨረታ ከተከፈተበት 60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ መሆን ይኖርበታል
ሎት- 2 (light Electric Vehicle 2) የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 520,000.00 /አምስት መቶ ሃያ ሺ ብር ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው በሲ.ፒ.ኦ ፤ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሆኖ ጨረታ ከተከፈተበት 60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ መሆን ይኖርበታል ̇
- ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱ በሚገኝበት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት በፋይናስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 73 የማይመለስ 500./አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
- ጨረታው አየር ላይ የሚውልበት ቀን 12/09/2018 ዓ.ም ፤
- ጨረታው የሚዘጋው፡-25/09/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ሆኖ በእለቱ ከሰዓት 9፡30 ይከፈታል።
- የሚቀርበው እቃ አይነትና ይዘት በጨረታ ሰነዱ የተገለጹ መስፈርቶችን አሟልቶ መቅረብ የሚችል፤
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ ዋናው መስሪያ ቤት በሚገኝበት አዲስ አበባ መሻለኪያ ከሸዋ ዳቦ ፊት ለፊት የቀድሞው አራተኛ ክፍለ ጦር ግቢ በአካል ወይም በስልክ 011 470 2063/ 011 470 2064 መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-06-02 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Railways Corporation
- Buyer TIN: 0004722443
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T12:18:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.