የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውኃና ኢነርጅ ቢሮ በመንግስት ኢመርጀንሲና በዩኒሴፍ የበጀት ድጋፍ በክልል ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር አብክመ/ውኢቢ/ግጨ/ዕግ/ቁጥር-005/2018

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውኃና ኢነርጅ ቢሮ በመንግስት ኢመርጀንሲና በዩኒሴፍ የበጀት ድጋፍ በክልል ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ በ2018 የበጀት ዓመት

  • ሎት 1. ለደጎሎ፣ ደብረታቦር፣ ዘጌ፣ ዘርባቢት፣ ቃጥዲኩሊ፣ ቅራቅር፣ አማኑኤል፣ መሻህ፣ ማርወለድ፣ ወይን እናት፣ ወፍ አርግፍ፣ ጨፋ ሮቢት፣ ገበዘ ማሪያም፣ ሉማሜ እንጅባራና ፍላቂት ገረገራ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ የፓምፖች፣መገጣጠሚያዎች፣ የራይዘር ፓይፕ እና የኬብል ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 2. ለወይን እናት፣ ገበዘ ማሪያም፣ ቢስጢማ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ የሶላርና አክሰሰሪዎች ዕቃ አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 3. ለሰኞ ገበያ፣ ቲርቲራ፣ ደላንታ፣ አጣዬ፣ ፈረደ ውሃ፣ ዋድላ መቄት፣ ሃራ፣ ደብረ-ዘቢጥ፣ ዱባባና ፈንድቃ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ የፓምፖችና አክሰሰሪዎች ዕቃ አቅርቦት ግዥ እንዲሁም
  • ሎት 4. ለሙገጭት፣ ዱባባና ፈንድቃ የሶላርና አክሰሰሪዎች ዕቃ አቅርቦት ግዥ ሕጋዊ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1.  በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. ተጫራቾች ዕቃውን /አገልግሎቶችን ለማቅረብ በዘርፉ (የኤሌክትሮ-ሜካኒካል ዕቃዎች አቅራቢነት) ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) ብቻ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃና ኢነርጅ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 27/23 ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ለሎት 1. ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር)፣ ሎት 2. ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር)፣ ሎት 3. ብር 450,000 (አራት መቶ አምሳ ሺህ ብር) እና ሎት 4. ብር 350,000 (ሶስት መቶ አምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክነካል ዋናና ሁለት ቅጅዎች እና ፋይናንሺያል ዋናና ሁለት ቅጅዎች በማሸግ ለየብቻ በታሸገ ፓስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለብቻ በፖስታ በማሸግ በእያንዳንዱ ፓስታ ላይ የድረጅቱን ፊረማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ሎት የገዥን ስም በመጻፋ በአማራ ውኃና ኢነርጅ ቢሮ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ግንቦት 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ደግሞ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን በዚሁ ቀን ጨረታው 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የሥራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ /ቅጽ/ መሰረት መሙላት ይኖርበታል።
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 226 24 60 /058 220 08 55 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የአብክመ ውኃና ኢነርጅ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-02 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የአብክመ ውኃና ኢነርጅ  ቢሮ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1,000 (አንድ ሽህ ብር)
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-21T07:57:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders