በአ/ብ/ክ/መ በጎንደር ከተማ አስተዳደር የማራኪ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም በጀት ለማራኪ ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ብሎክ ግንባታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአ/ብ/ክ/መ በጎንደር ከተማ አስተዳደር የማራኪ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም በጀት ለማራኪ ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ብሎክ ግንባታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1ኛ, የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2ኛ. ተወዳዳሪዎች እስከ 2013 ዓ.ም ማጠናቀቂያ ድረስ ባከናወኗቸው ተግባራት የመልካም የስራ ውጤት ማቅረብ የሚችሉ።

3ኛ. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ሌሎች የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4ኛ. ተጫራቾች 1% ሲፒኦ በባንክ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ።

5ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 ብር ማራኪ ጤና ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

6ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ግንባታ አሸናፊው ከተረጋገጠ በኋላ ለ5 የስራ ቀናት ሁሉም ተረጋግጦ በ5 ተከታታይ ቀናት ውል መውሰድ የሚችል።

7ኛ. ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በኦርጅናል ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ በግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን በ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት አለባችሁ።

8ኛ. ተጫራቾች ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ማህተም እና ቀን፣ ሙሉ ስምና አድራሻ በመግለፅ በቀን 13/09/2018 ዓ.ም እስከ 30/09/2018 ዓ.ም ማስገባት ይችላሉ።

9ኛ. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማ/ጤ/ጣ/ግ/ፋ/ን/ አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በቀን 1/10/2018 ዓ.ም በተዘጋጀው ሳጥን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

10ኛ. መስሪያ ቤቱ ስለጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ከላይ በተገለፀው መስፈርት መሰረት ማንኛውም አቅራቢ መወዳደር ይችላል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ

የማራኪ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-06-08 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Maraki Health Center
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 50.00 ብር
  • Published: May 21, 2026
  • Posted at: 2026-05-21T08:00:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders