በማዕከላዊ ጐንደር ዞን የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ G+1 ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ጐንደር ዞን የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

ሎት1. G+1 ቢሮ ግንባታ መሃንዲስ ባወጣዉ የስራ ዝርዝር እና ዲዛይን መሰረት የእጅ ዋጋ እና ጥሬ እቃን ጨምሮ ጥቅል ዋጋ በማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

 የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፡፡
  3.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሰርትፊኬት ያላቸዉ፡፡
  5.  ሁሉም ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና በህንጻ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ የሆኑ፣ በዘመኑ የታደሰ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1500 (አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 0.5 በመቶ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ከ90 ቀናት ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከኮሌጁ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ጋራንቲ (ቢድ ቦንድ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጠ/ጤ/ሣ/ ኮሌጅ በግዥና/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ31ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል፣ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. የስራዉ ዝርዝር ወይም ሰፔስፊኬሸን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲ ሆን ዉድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡፡
  12. በጨረታው ላይ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 058 448 02 34 ይደዉለው ወይም ጠዳ ጤና ሳ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚያስደርጉ ሁኔታዎች፡፡

  1.  ጨረታውን ሆን ተብሎ ለማደናቀፍ የሚደረግ የዋጋ አሞላል ከውድድር ውጭ ይደርጋል፡፡
  2. ትክክለኛ የጨረታ ሰነዶችን ኦርጅናልና ኮፒ የፖስታ አስተሻሸግ ያልተከተለ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡የዚህን አዋጅ ለማስፈፀም የወጣውን መመሪያ ሲጥስ ወይም በአዋጁ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን እና በጨረታ ሰነድ የተመለከቱትን መሰረታዊ ጉዳዮች ሣያሟሉ ሲቀር፡፡
  3. የተለየ አስተያየትን ለማግኘት ወይም ጨረታውን ለማሸነፍ ለማንኛውም ባለስልጣን ወይም ሰራተኛ መደለያ መስጠቱ ወይም የመስጠት ሀሳብ ማቅረቡ በአሣማኝ ሁኔታ ሲረጋገጥ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  4. ተወዳዳሪው በጨረታው ሰነድ ላይ የማጭበርበር ተግባር መፈፀሙ ወይም ከሌላ እጩ ተወዳዳሪ ጋር መመሳጠሩ በአሣማኝ ሁኔታ ሲረጋገጥ፡፡
  5. ተወዳዳሪው የመጫረቻ ሰነዱን በጨረታ ሳጥኑ ካስገባ በኃላ እራሱን ከጨረታ ለማግለል ከፈለገና ጨረታው ከመዘጋቱ ቀንና ሰዓት በፊት የማግለያ ሀሳቡን በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ካላስገባ ፣ቀደም ሲል በተሳተፈበት የመንግስት ጨረታ የገባውን ግዴታ ያልፈፀመ ከሆነ፣የጨረታ ማስከበሪያ እንዲያሲዝ የተጠየቀውን በጨረታ ማስታወቂያዉ በተገለፀዉ ዓይነት ያላስያዘ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በማወዳደሪያ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ የተገኘ፣የተሞላው ዋጋ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ ለማንኛውም መረጃ በስልክ ቁጥር 058 448 02 34 ደውለው መጠየቅ ይቸላሉ፡፡

የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛዉ ቀን 4፡00
  • Bid opening: 2026-06-17 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛዉ ቀን 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Teda Helath Science College
  • Bid bond: 0.5 በመቶ
  • Bid document price: 1500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-21T08:04:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders