በምዕራብ ወለጋ ዞን የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዝብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዘመን በነጆ ለከተማ አስተዳደር ባለ 5 ፎቅ ሕንፃ B+ G+5 በሙሉ ኮንትራክት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዝብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዘመን በነጆ ለከተማ አስተዳደር ባለ 5 ፎቅ ሕንፃ B+ G+5 በሙሉ ኮንትራክት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-
1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. ተጫራቾች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም ከኦሮሚያ ኮንስትራክሸን ቢሮ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዓመቱን ግብር ስለመክፈለቸው ኮኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ከፌዴራል ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
7. በጨረታው የሚሳተፉ ኮንትራክተሮች BC-2 ወይም GC-3 እና ከዚያ በላይ ያላቸው መሆን አለበት።
8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዝብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቁጥር 7 ቀርበው መግዛት ይቻላል።
10. ተጫራቾችለሚያቀርቡት ጨረታ የቴክኒክ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ፤ እንደዚሁም የፋይናንስ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመጨራሻ የቴክኒክ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ አድርጎ የፋይናንስ ሰነዱንም ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ በነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዝብ ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
11. የፋይናንስ ሰነድ የሚከፈተው የቴክኒክ ግምገማ ካለፉ ብቻ ይሆናል፡፡ ቴክኒክ ግምገማ ከአለፉ የፋይናንስ ሰነዶቻችሁ ሳይከፈት ይቀራሉ።
12. ማንኛውንም የሀሰት ማስረጃ ያቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል።
13. ተጫራቾች ባለፉት አምስት ዓመታት በክልላችን ወይም በዞናችን የ100,000.000 (አንድ መቶ ሚሊዮን)ና ከዚያ በላይ የሠራበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጋር መሆኑን መግለጽ አለባቸው።
15. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣባት ቀን ጀምሮ በ30ኛው የሥራ ቀን በ4፡30 በጨረታው ሣጥን ታሽጎ በዚያው ቀን በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ከሆነ ወደሚቀጥለው ቀን ይተላለፋል።
16. ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ከታወቀ ድርጅት ኢንሹራንስ በሁኔታው ላይ የተመሠረተ ማስያዝ ይኖርበታል።
17. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ ይኖርበታል።
18. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
19.ተጫራቾች በሰነዶቻችሁ ላይ ስማቸውን፤ ሙሉ አድራቸውንና ስልክ ቁጥራቸውን በትክክል ጽፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው።
20. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች የጨረታውን ግዴታ ባይወጣ ለውል ማስከበሪያ 10% ያስያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤት ገቢ ይሆናል።
21. ተጫራቾች ቢገኙም በይገኙም ጨረታውን አያስተጎጎልም
22. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፡-
ስልክ ቁጥር 0917093749፣ 0922429665,0917299570
የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዝብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው የሥራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-25 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው የሥራ ቀን በ5፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Nejo Woreda FEDB
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T07:33:37.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.