የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የአርቴፊሻል ሳር ምንጣፍና ፖስቲሽ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
NCB 005/2018
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የቀረበውን ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ NCB 005/2018 አወዳድሮ የአርቴፊሻል ሳር ምንጣፍና ፖስቲሽ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ቲን ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተቀመጠው ቀንና ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
3.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቴክኒካልና ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ፤ ፋይናንሽያል ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በኢንቨሎፕ በማድረግ መቅረብ አለበት:: የኮፒ ሰነዶች ከኦሪጅናል ሰነዱ ጋር በአይነትም ሆነ በብዛት ተመሳሳይ መሆን አለበት። የጨረታውን ስምና ቁጥር በመግለጽ በኮርፖሬሽኑ ግዥ ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሽጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል።
6. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011-517-2521/11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ።
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሸን
Tender details
- Deadline: 2026-06-06
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30
- Bid opening: 2026-06-06 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡45
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Broadcasting Corporation
- Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር)
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T07:38:54.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.