የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ግ.ጨ/ኢ.ኢ.ኮ/15/2018
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል:: በዚሁ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናችውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለኪራይ አገልግሎት የሚያቀርቧቸው ተሽከርካሪዎች የመድን ሽፋን ማስረጃና የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር/ሊብሬ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00/ሰላሣ ሺህ ብር/ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የቴከኒክ ሠነድ እና የፋይናንሻያል ሠነዳቸውን ለየብቻ በማዘጋጀትና በማሸግ ዋና ከኮፒ ጋር በአንድ ፖስታ ውስጥ በሰም አሸገው እስከ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
1. ጨረታው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል።
2. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ብር 50,000.00/ሀምሳ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው።
4. ኮርፖሬሽኑ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ህንጻ ቁጥር : 1 4ተኛ ፎቅ፣ የግዥ ንብረትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬከተር ቢሮ ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው ዋና መንገድ ዳር የድርው ኢምፔሪያል ሆቴል በመባል በሚጠራው አካባቢ አዲሱ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ አጠገብ
ቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05፣
ስልክ ቁጥር +251 118 72 07 22
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-16
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-16 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Engineering Corporation
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T07:48:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.