የመንዝ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን ኃ.የተ አግሮ ኬሚካል፣ መርጫ መሳሪያ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን መጌራ ምድር ወረዳ የሚገኘው የመንዝ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን ኃ.የተ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር የተዘረዘሩትን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. አግሮ ኬሚካል
2. መርጫ መሳሪያ
ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን ምርቶች ከሀገር ውስጥ ገበያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች በወጣው ማስታወቂያ መሰረት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን በጨረታው ለመሳተፍ
1. ከላይ በተዘረዘሩት የንግድ ዘርፎች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ያላት።
2. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት
3. የንግድ መለያ ቁጥር /TIN/ ኮፒ
4. የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ከሚመለከተው ገቢ ሰብሳቢ ተቋም ማረጋገጫ ወይም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
7. ለመግዛት የሚያቀርቡትን ምርት ዝርዝር መግለጫ የያዘ ጨረታ ሰነድ ከዩኒዬኑ መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በዩኒዬኑ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000074206054 በመክፈል በመ/ሜዳ ከተማ ከኢትዮ ቴሌኮም መስሪያ ቤት ጀርባ በሚገኘው በመንዝ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን ኃ.የተ ጽ/ቤት ወይም ደ/ብረሃን ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ቢሯችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እና ለሚሞሉት ዋጋ 2% ሲፒኦ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ በሁለት ፈራሚ የተረጋገጠ በአ/አበባ፣ ደ/ብርሃን እና መ/ሜዳ ባሉ ባንኮች በዩኒዬኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን ዶክመንት ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በሁለት ፖስታዎች ተለያይቶ በአንድ ፖስታ ታሽጎ በመ/ሜዳ ከተማ በሚገኘው በመንዝ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን ኃ.የተ ጽ/ቤት ወይም ደ/ብረሃን በሚገኘው ቢሮአችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ እስከ አስረኛው ቀን ስምንት ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል።
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ሜዳ ከተማ በሚገኘው በመንዝ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን ኃ.የተ ጽ/ቤት ወይም ደ/ብረሃን በሚገኘው ቢሮአችን በአስረኛው ቀን ከቀኑ ስምንት ሰዓት (8፡00) ጨረታው ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ሜዳ ከተማ በሚገኘው በመንዝ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን ኃ.የተ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ; 0116850422/0116850457/0920854560 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ማሳሰቢያ፦ የጨረታ ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ የግዥ አይነት የነጠላ ዋጋ እንጂ በሎት ወይም በጥቅል አለመሆኑን ተረድታችሁ ዋጋችሁን እንድትሰጡ እናሳስባለን።
የመንዝ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን ኃ.የተ
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ ስምንት ሰዓት (8፡00)
- Bid opening: 2026-06-02 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ ስምንት ሰዓት (8፡30)
- Region: Amhara
- Publishing entity: የመንዝ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን ኃ.የተ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር)
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T07:51:32.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.