Crop protection and pest control
የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የስንዴ ዘር ከተከማቸበት ከተማ ወደ ሚፈለገዉ ቦታ ለማጓጓዝ፣ የሰብል ጥበቃ ቁሳቁስና የተለያዩ ኬሚካሎች፣ የዘር ማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ፣ የደንብ ልብስ፣ የላብራቶሪ ማቴሪያልና የዘር ታግ ህትመት ለመግዛት እና የተለያዩ ለዘር የማይሆኑ ሰብሎች፣ የተለያዩ ብጣሪዎች እና ያገለገሉ ጆንያዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የስንዴ ዘር ከተከማቸበት ከተማ ወደ ሚፈለገዉ ቦታ ለማጓጓዝ፣
- የሰብል ጥበቃ ቁሳቁስና የተለያዩ ኬሚካሎች፣
- የዘር ማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ፣
- የደንብ ልብስ፣ የላብራቶሪ ማቴሪያልና የዘር ታግ ህትመት ለመግዛት እና
- የተለያዩ ለዘር የማይሆኑ ሰብሎች፣ የተለያዩ ብጣሪዎች እና ያገለገሉ ጆንያዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ቢሮ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመኪና ባለቤትነት ማረጋገጫ እና የመጫን ችሎታ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ ለማቅረብ ፈቃድ የተሰጠዉና ከ2 ወር ባልበለጠ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የደረቅ ጭነት ማመላለሻ መኪናዎች ያሉትና የመኪናዎችን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ከዋናው ጋር የተረጋገጠ ኮፒ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ሲጠየቅ ዋናውን ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት ባሕር ዳር ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
- የተለያዩ ንፁህ ሰብሎች የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፣
- ግዠዉን ባህር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ይመልከቱ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በአለ በጅምላ ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ 10ኛው ቀን ላይ (ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን) በ8.30 ይከፈታል፡፡
- ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 6002 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 8415/09 18 01
69 35 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-08-13
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-13 14:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን ላይ (ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን) በ8.30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Seed Enterprise
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር ለአንድ ሎት
- Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T11:53:27.000Z