በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ሞተርሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የሸያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 11/2018
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ሞተርሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 9/2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
1. የኤጀንሲው አድራሻ ፤አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ / የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት/ ጫፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር -02 መግዛት ይችላሉ።
2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 –10፡00 ሰዓት ብቻ ነው።
3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ሰኔ 9/2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30–10፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ሰኔ 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-1-8340-636
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-06-17
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-17 11:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia National Regional State Regional State Public Procurement and Property Disposal Agency
- Bid bond: 20% ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T08:30:29.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.