የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን Rugged Handheld GPS with Compass and Barometric Altimeter እና የቪዲዮ እና የፎቶ ማለትም “DUAL” የሆነ ካሜራ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጂፒኤስ ግዥ እና የካሜራ ደግሞ በድጋሚ ግዢ ለመፈጸም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ደኢመባ ቁጥር 12/2018

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

በሎት አንድ Rugged Handheld GPS with Compass and Barometric Altimeter ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት እና በ ሎት ሁለት ደግሞ በድጋሚ የቪዲዮ እና የፎቶ ማለትም “DUAL” የሆነ ካሜራ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ የቴክኒክ እና ፋይናንሻሉን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስከበሪያው ደግሞ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለየ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውንና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በትክክል ማስፈር አለባቸው።

3.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእየአንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ከባለሥልጣኑ ዋና ቢሮ ቁጥር --- መውሰድ ይችላሉ።

4. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

5. ተጫራቾች በእንግሊዘኛ የተጻፈውን የቴከኒክ ዝርዝር መግለጫ በሚጠይቀው መሠረት መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ይህንን ያልሞሉት የቴከኒክ ዝርዝር መግለጫ እንዳልቀረበ ተቆጥሮ የማቅረብያ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው መሠረት

.

የዕቃው ዓይነት

 

Qty

የጨረታ ማስከበሪያ

1

Rugged Handheld GPS with Compass  and Barometric Altimeter

08

13,500.00

2

DUAL CAMERA

01

25,000.00

የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም ከኢንሹራንስ ዋስትና በቀር በግዥ መመሪያው ላይ ባሉ አማራጮች በፈለጉት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።

8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ። ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳሉ፡፡ ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።

9. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት።

10. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ድርጅት መሆኑ ከተገለፀለት አምስት /5/ ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና /Performance Bond/ 10% በባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ በማቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል።

ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተስውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡-

ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም

የስልክ ቁጥር 046 131 5012/ 09 23 69 00 85

ዲላ ኢትዮጵያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት መንገዶች ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-06
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-06 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: South Ethiopia Regional State Roads Authority
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: May 22, 2026
  • Posted at: 2026-05-22T08:51:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders