ዋን ኤከር ፈንድ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአቮካዶ ዘር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል

★ Featured

Description

የአቮካዶ ዘር ለመግዛት የወጣ ጨረታ

ዋን ኤከር ፈንድ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአቮካዶ ዘር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል። ይህንን ዘር ተጠቅመን ችግኞችን በማምረት አርሶ አደሮች ገቢያቸውን ለማሳደግ፣ ኢኮኖሚያቸውን ለማረጋጋት እንዲሁም ከባቢ አየርን ለማሻሻል ለሚፈልጉ አርሶ አደሮች ለማሰራጨት እንጠቀምባቸዋለን።

● የሚያስፈልገው የአቮካዶ ዘር ፦

○ ጠቅላላ የሚያስፈልገው መጠን 2,280 ኪ.ግ የአቮካዶ ዘር ሲሆን፥ በአንድ ኪሎግራም 28 ዘሮች እንዳሉ ይገመታል ፤ ጠቅላላ የሚያስፈልገው የዘር ብዛት 63,840 ነው።

○ ይህንን ለማግኘት 9,120 ኪ.ግ የአቮካዶ ፍራፍሬ ያስፈልጋል ተብሎ ይገመታል።

● ተጫራቹ ዘሩን ከፍራፍሬው በመለየት እንዲያዘጋጁ ይጠበቃል።

● ተጫራቹ ዘር መሸጥ ካልቻለ እና ፍራፍሬ መሸጥ ብቻ ከፈለገ ተጫራቹ አሁንም መጫረት ይችላል ነገር ግን ተመራጭነቱ ይቀንሳል፡፡

●ተጫራቾች በጨረታው ወቅት የአቮካዶ ዛፎችን በባለሙያዎች እንዲጎበኙ እና ጥራታቸውን እንዲመለከቱ ፈቃደኛ መሆን መቻል አለባቸው። የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ ባለሙያው የእናት ዛፍ አመራረጥን፣ ዘሩን ከፍራፍሬው የመለየት ሂደቱን ተመልክቶ አቅጣጫ ይሰጣል።

●  በተጨማሪም ተጫራቹ ዘሮችን በ Annex 1 ላይ ወደ ተዘረዘሩት ቀበሌዎች (የTNO ችግኝ ጣቢያዎች) ያቀርባል።

● 2 የዋጋ አሰጣጥ አማራጮች አሉ። ወይ ተጫራቹ ሙሉ ለሙሉ ለተመረተ ዘር በኪሎ የመጨረሻውን ዋጋ ይሰጣል ወይም ፍሬውን ለማቀነባበር ከሚወጣው ዋጋ ጋር በኪሎ ግራም ይሰጣሉ።

● አቅራቢው ከእያንዳንዱ መሰብሰብያ ኩንታል ወይም ባግ 100% የአቮካዶ ፍሬ እንደ ናሙና ተወስዶ ከዚህ በታች ባለው የጥራት ማረጋገጫ መስፈርት መሰረት እንዲመረመር ፈቃደኛ መሆን አለበት፡

○ መካከለኛ የብስለት ደረጃ (ያልበሰለ ወይም ከመጠን በላይ ያልበሰለ)

○ መካከለኛ መጠን

○ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎች ያልሆኑ

○ በዘሩ ሽፋን ላይ የበሽታ/የፈንገስ ምልክቶች የሌለባቸው

○ ያልረጠበና የደረሰ

ከዘር ጥራት ፍተሻ ሂደቱ የተገኘው ውጤት ከ85% በታች ከሆነ ሁሉም ዘሮች ውድቅ ይሆናሉ።

እባክዎን የሚከተለውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ይሙሉ፣ ከዚያ ይፈርሙበትና ማህተም ያድርጉበት፣ እና ወደሚከተለው የኢሜል አድራሻ ብቻ ይላኩ፡፡

● ኢሜይል ethiopia.bidsubmissions@oneacrefund.org

● ማንኛውንም የዋን ኤከር ፈንድ ሰራተኛ በጉቦ ለመጠቀም መሞከር ዘላቂ እገዳን ያስከትላል። ሁሉም ጨረታዎች እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ድረስ መቅረብ አለባቸው።

ጥያቄ

መልስ

የተዘጋጀ የአቮካዶ ዘር ዋጋ በኪሎግራም?

 

መሰብሰብ የሚጀምሩት መቼ ነው?

 

ለዘር በኪሎግራም ዋጋ መስጠት ካልቻሉ፣ የፍራፍሬው ዋጋ በኪሎግራም ስንት ነው?

 

በ Annex 1 ላይ ለተዘረዘሩት ቀበሌዎች (የ TNO የችግኝ ጣቢያ) የወጣውን ዘር ለማቅረብ ፈቃደኛ ነዎት?

 

አዎ ከሆነ፣ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለአቮካዶ ዘር በኪሎግራም ዋጋዎ ስንት ነው?

 

አዎ ከሆነ፣ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለአቮካዶ ፍሬ በኪሎግራም ዋጋዎ ስንት ነው?

 

የእናት ዛፎቹ የት ይገኛሉ (ቀበሌ እና ወረዳ)?

 

አንድ ባለሙያ ምርጫውን፣ አሰባሰቡን እና አወጣጡን እንዲታዘብና መመሪያ እንዲሰጥ ፈቃደኛ ነዎት?

 

ውል ከተፈረመ ከስንት ጊዜ በኋላ መሰብሰብ መጀመር ይችላሉ

(ቶሎ ቢሆን ይመረጣል)?

 

ውል ከተፈረመ በኋላ 2,280 ኪ.ግ ዘርን ሙሉ በሙሉ ሰብስበው፣ አውጥተውና አዘጋጅተው ለመጨረስ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅብዎታል (ቶሎ ቢሆን ይመረጣል)?

 

● ዋን ኤከር ፈንድ ከማንኛውም ሻጭ የተቀበለውን ምርጥ ዋጋ ከሁሉም ተጫራቾች ጋር የመጋራት መብት አለው።

● ዋን ኤከር ፈንድ በማንኛውም ምክንያት ማንኛውንም ሻጭ አለመቀበል ወይም ማጽደቅ መብት አለው።

● ዋን ኤከር ፈንድ የኮንትራት ፊርማ ከመደረጉ በፊት ይህንን ጨረታ በማንኛውም ጊዜ ሊሰርዝ ይችላል።

● ዋን ኤከር ፈንድ ለተለያዩ ሻጮች የተለያዩ መጠኖችን ሊሰጥ ይችላል። OAF የተወሰነ መጠን ከመግዛትም ሊታቀብ ይችላል። መጠኖች የመጨረሻ አይደሉም፣ እና የመጨረሻ ኮንትራቶች ከመፈረማቸው በፊት ሊለወጡ ይችላሉ።

● ዋን ኤከር ፈንድ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ወይም ማንኛውንም የጨረታውን ገጽታ የማሻሻል እና ማንኛውም አቅራቢ ያቀረበውን ጨረታ ለማንኛውም ውሳኔ እና ድርጊት ምክንያት ሳያቀርብ በማንኛውም ምክንያት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Annex 1፡ የሚቀርብባቸው ቀበሌዎች ዝርዝር

Woreda

Kebele

Woreda

Kebele

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Boloso Sore

Afama Mino

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Damot Gale

Aro Wegera

Dache Gofara

Mokonisa weygie

Gido Homba

Wandara Gale

Shuye Homba

Zegerie

Sore Homba

Damot Mokonisa

Tiyo Hembecho

Damot Boloso

 

Konasa pulasa

 

Obe Jage

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Damot Sore

Dogie Anchicho

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Damot Woyde

Sake Mazegaja

Sore Kelena

Girara Mazegaja

Anchiche Choqarie

Mundaja Sakie

Dembe Zamine

Koyo Sakie

 

Dawiee Sakie

 

Ade Dawi Mundega

 

Tora Wlisho

 

Demba Gerara

 

Kindo Koyo

 

Offa

Kebele 1

Damot Pulasa/ offa

 

Kebele 3

 

Damot Plassa

Kebele 2

 

 

ማስታወሻ፡ አቅራቢው ዘሩን ከላይ በተዘረዘሩት በእያንዳንዱ ቀበሌ በሚገኘው የTNO ጣቢያ እንዲያቀርብ እንፈልጋለን። በተጨማሪም Kebele 1, Kebele 2 እና kebele 3 ዉል ከመፈራረማችን በፊት የምናሳዉቅ መሆኑን እንገልጻለን።

ስም------------------------                                         ፊርማ------------------------ 


Tender details

  • Deadline: 2026-05-28
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-05-28 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: One Acre Fund
  • Buyer TIN: 0041750397
  • Buyer address: Yeka Sub City, Woreda 8, Level 5, Building Opposite Misrak Polytechnic College, Addis Ababa, Ethiopia Or Kebele 13, Bahir Dar, Amhara Region(Bahir Dar office)
  • Published: May 22, 2026
  • Posted at: 2026-05-22T11:57:19.000Z
  • Buyer website: https://oneacrefund.org/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders