ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ የህትመት ጥሬ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 007/2018

ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ የህትመት ጥሬ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

1ኛ. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ፣

2ኛ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

3ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣

4ኛ. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣

5ኛ. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣

6ኛ በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ ገፅ በአቅራቢነት ተመዝጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

7ኛ. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር አምስት መቶ (500.00) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ወሎ ሰፈር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 26 በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 2% በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣

9ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስረከቢያ ጊዜውን መጥቀስ አለባቸው፣

10ኛ. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ድርጅቱ መጋዘን ድረስ ማድረስ አለባቸው፣

11ኛ. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው የሥራ ቀን እስከ ከረፋድ 3፡30 ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በወጣ በ 11ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

12ኛ. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል
ስልክ ቁጥር፡-0114 42 64 80
ብራና ማተሚያ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-04
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ8፡00
  • Bid opening: 2026-06-04 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ8፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Branna Printing Enterprise
  • Buyer address: ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 23, 2026
  • Posted at: 2026-05-23T07:06:37.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders