የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የአቡካዶ ችግኝ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የአቡካዶ ችግኝ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 448/18

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለብሔራዊ አቡካዶ ልማት ፕሮግራም የሚውል የአቡካዶ ችግኝ ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

/

 

የዕቃው አይነት

ሎት

 

መለኪያ

 

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ

የሚታሸግበት ሰዓት

ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ

1

የአቡካዶ ችግኝ

ሎት-1

በቁጥር

15,000

 

50,000.00

 

በ 16 ኛው ቀን 400 ታሽጎ በዕለቱ 410 ይከፈታል

///ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ

በንግድ ስራ ዘርፍ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት መዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
  • በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ-ፒ-ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው
  • ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ እስከ 15ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 300 ( ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ይህ የጨረታ የቴክኒካልና ፋይናሻል ኦርጅናልና ኮፒ የማጫረቻ ሰነዶች በአንድ ፖስታ በማዘጋጀት በ 16 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡10ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
  • ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ለሆነ ግዥዎች ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  • ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  • የጨረታው ሳጥን መክፈቻ በ6ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  • ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል።
  • ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለበለጠ መረጃ 046 131–0134 ይጠቀሙ።

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን በ4፡00
  • Bid opening: 2026-06-08 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን በ4፡10
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Southern Ethiopia Regional Government Agriculture Office
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 23, 2026
  • Posted at: 2026-05-23T07:24:35.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders