የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት በስሙ ተመዝግበው የሚገኙትን ተሽከርካሪ መኪናዎች በሕጋዊ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት በስሙ ተመዝግበው የሚገኙትን ተሽከርካሪ መኪናዎች በሕጋዊ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ።

1 ምኒባስ (አባ ዱላ) 1

2. ምኒባስ (5L) 1

3. ኃይሉክስ (ዳብል ካፕ) 1

4 ኤንትሪ ቦት የተጫነበት 1

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መኪናዎች በጨረታ መግዛት ለምትፈልጉ በተጫራች በኩል መሟላት ያለበት መሥፈርት ፡-

የጨረታ ሰነድ ሽያጭ

  • ተራቾች የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሽህ ብር) ከደብሩ ጽ/ቤት መግዛት አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸዉ።
  • የመግዣ ዋጋ በአንድ መኪና ለብቻ ወይም በጠቅላላ ሊቀርብ ይችላል ፖስታ ላይ የገንዘቡ መጠን በግልጽ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለበት።

የጨረታ ሰነድ አቀራረብ

  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን በታሸገ ፖስታ (ኢንቨሎፕ) በተጠቀሰው አድራሻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  •  ጨረታው ማስታዋቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ይሆናል።
  • ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ጨረታው ይከፈታል።
  • በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ሰነዱ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

የቴክኒክ ሁኔታ

  • ተሸከከርካሪዎች አሁን ላይ ባሉበት ሁኔታ የሚሸጡ ሲሆን ገዳሙ ከሽያጭ በኋላ ለሚፈጠረው ማነኛውም የቴክኒክ ችግር ተጠያቂ አይሆንም።
  • ከጨረታ በፊት ቴክኒካል ሁኔታ ማረጋገጥ የሚቻል ሲሆን የባለሞያ ክፍያ በተጫራች በኩል ይሆናል።
  • ተወዳዳሪዎች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መኪናዎቹን ማየት ይችላሉ።

የክፍያ ሁኔታ

  • አሸናፊ ተጫራች የቀረበውን ገንዘብ ውጤቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 100 % በገዳሙ አካውንት የመክፈል ግዴታ አለበት።

« ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር

ማሳሰቢያ፡- የገዳሙ ሰበካ ጉባኤ አስ/ጽ/ቤት የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 033 336 00 21 (09 11 78 81 86) ይደውሉ

አድራሻ ቅ/ላሊበላ ደብረ ዘይት ቀበሌ ከደብሩ አዲሱ ጽ/ቤት (መካንዝባ )

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም


Tender details

  • Deadline: 2026-06-09
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-09 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ አስ/ጽ/ቤት
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: May 23, 2026
  • Posted at: 2026-05-23T08:34:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders