በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት የቁም ደን ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OFWE/GU-17/2018
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ጂማ ቅ/ጽ/ቤት በለጠ ጌራ ፤ሲግሞ ሰጠማ እና በቢያ ፎላ ድስትሪክቶች፤ ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት መጋዳ እና ቦሬ ድስትሪክቶች ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጃሎ ሙክታር ድስትርክት፤ ምዕራብ ወለጋ፤ ቄለም ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ድስትሪክቶች ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ የ”Grevillea robusta” እና የ”Pinus” ግንድላ፤ እንዲሁም በነዚሁ ድስትርክቶች ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ፤ በተጫማሪም በጂማ ቅ/ጽ/ቤት በቢያ ፎላ ድስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ጂማ ቅ/ጽ/ቤት ነ/አበልት ድስትርክት፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ገ/ድዴሳ ድስትሪክት ፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጋራ ሙለታ ዲስትሪክት፤ ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ቦሬ እና ዋዳራ ድስትሪክቶች ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ የ”Grevillea robusta” እና የ”Pinus” ግንድላ እንዲሁም በነዚሁ ድስትርክቶች ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TIN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ፤ ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት አዶላ ከተማ፤ ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ እና ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ጊምቢ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል።
3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፋትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
5. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 124 0249 በመደወል ማጠየቅ ወይም ድህረ-ገፅ “ www.oromiaforest.et ” ማጎብኘት ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል
- Bid opening: 2026-06-08 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል
- Region: Oromia
- Publishing entity: Oromia Forest and Wild Life Enterprise
- Buyer address: Addis Ababa, Arada Sub-City, Woreda 07, AAround Kebena OiLibiya
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: May 24, 2026
- Posted at: 2026-05-25T07:16:08.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.