የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር ባስገነባው የገበያ ማዕከል ህንጻ ውስጥ የቢሮ ፓርቲሽኖችን በመስታወት እና ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የቢሮ ፓርቲሽን ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ

የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር ባስገነባው የገበያ ማዕከል ህንጻ ውስጥ የቢሮ ፓርቲሽኖችን በመስታወት እና ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

1. በአልሙኒየም ሥራ እና ደረጃ 5 ጠቅላላ ወይም በህንጻ ሥራ ተቋራጭ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት።

2. የቫት እና የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN)።

3. የ2017 ዓ.ም ከግብር ዕዳ ነፃ የሆኑበትን ሰርተፊኬት።

4. ለሚቀበሉት ክፍያዎች ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ።

5. በዘርፉ ተሰማርተው ለሰሩት ሥራ በቂ የሥራ ልምድ ማቅረብ እና የሰሩትን ሥራም ማሳየት የሚችሉ።

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የሰነዳቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ በመያዝ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ከማህበሩ ጽ/ቤት ብር 1000 ከፍለው በመውሰድ ዋጋቸውን ሞልተው ለጨረታ ማስከበርያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ብቻ በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከታች በተገለፀው ሰዓት የሰነዶቻቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል

አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ቅናሽ ዋጋ የመምረጥ ግዴታም የለበትም።

ማስታወሻ፡-

  • አድራሻ፡- ኮልፌ አጠና ተራ ከቴሌው ጀርባ የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ ማህበር ብሎክ 2 አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4
  • የጨረታውን ሰነድ መውሰድ የሚቻለው ከጠዋት 2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 10፡30 ብቻ ይሆናል

ስልክ 09 32-08-03-77 ወይም 09-12-05-47-92

የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-10
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-10 15:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስተኛው ቀን 9፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T07:20:37.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders