የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ህንጻ ማስገንባት ይፈልጋል
Description
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለማሰራት 01 ቀበሌ ከሌ ጀ ሃይሉ ከበደ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅድመ መደበኛ ት/ቤት ህንጻ ግንባታ ስራ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ BC & GC ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
|
ተቁ
|
የግንባታው አይነት
|
የጨረታ ማስከበርያ ብር
|
|
1 |
01 ቀበሌ ከሌ/ጀ ሃይሉ ከበደ ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅድመ መደበኛ ት/ቤት ህንጻ ግንባታ |
280,000.00
|
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. በርፉ በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የሞያ ፈቃድ ያላቸው፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ያላችው፣
4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታስክ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. የግንባታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ያገኙታል፣
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያአንዳንዱ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/አስ/ር ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይቻላል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግንባታ ከላይ በተገለጸው ገንዘብን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብን ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ለተከታታይ 60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጅበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን ዘወትር በስራ ሰአት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በ 22ኛዉ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል በዚሁ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፣
11. የሂሳብ ስሌት /አርትሜቲክ ቸክ/ በግዥ ፈጻሚዉ መ/ቤቱ ባለሞያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫራቾች የሚቀርበዉ የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፣
13. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ጊዜና ሰአት ይከፈታል።
14. ማንኛውም ተጫራች ላሸነፈው ፕሮጀክት ሁሉንም ለስራ የሚያስፈልጉ የማቴርያል አይነቶች ቴስት በራሱ ወጭ ከሚመለከተው ቦታ ወስዶ አሰርቶ የማምጣት ግዴታ አለበት።
15. አከባቢ ና ማሀገራዊ የተጽእኖ ማቃለያ እቅድ እና የአከባቢ ደህንነት የትግበራ መመርያ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆን አለበት፡
16. ማንኛውም ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር በአዲሱ በተሻሻለዉ መመርያ መሰረት ተገዥ መሆን አለበት።
17. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 033 540 7058 በመደዎል ማግኘት ይችላሉ። የሰቆጣ ከተማ አስ/ር/ ከ/መ/ ል/ ጽ/ ቤት
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጅበት ቀን ጀምሮ በ22ኛዉ ቀን 4፡00
- Bid opening: 2026-06-15 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጅበት ቀን ጀምሮ በ22ኛዉ ቀን 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Sekota City Administration Urban Infrastructure Development Office
- Bid bond: 280,000.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: May 24, 2026
- Posted at: 2026-05-25T07:23:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.