የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር ባስገነባው ህንጻ ውስጥ ያለውን ቢሮ የውስጥ ELV (Extra low Voltage System) እና የካሜራ ዝርጋታ የዲዛይንና ግንባታ (Design Build) ሥራውን ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የቢሮ ውስጥ የኔትወርክ እና ካሜራ ዝርጋታ ጨረታ

የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር ባስገነባው ህንጻ ውስጥ ያለውን ቢሮ የውስጥ ELV (Extra low Voltage System) እና የካሜራ ዝርጋታ የዲዛይንና ግንባታ (Design Build) ሥራውን ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾችን በ ELV System Integration ወይም IT ላይ ተሰማርተው የ2018ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያላቸው

2. የቫት እና የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN)፤

3. የ2017 ዓ.ም ከግብር ዕዳ ነፃ የሆኑበትን ሰርተፊኬት፤

4. ለሚቀበሉት ክፍያዎች ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፤

5. በዘርፉ ተሰማርተው ለሰሩት ስራ በቂ የስራ ልምድ ማቅረብ እና የሰሩትን ስራም ማሳየት የሚችሉ

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የሰነዳቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ በመያዝ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ከማህበሩ ፅ/ቤት በመውሰድ ዋጋቸውን ሞልተው ለጨረታ ማስከበርያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ብቻ በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከታች በተገለፀው ሰዓት የሰነዶቻቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል

አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ቅናሽ ዋጋ የመምረጥ ግዴታም የለበትም።

ማስታወሻ

  • አድራሻ ኮልፌ አጣና ተራ ከቴሌው ጀርባ የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር ብሎክ 2 አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4፤
  • የጨረታውን ሰነድ መውሰድ የሚቻለው ከጠዋት 2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 10፡30 ብቻ ይሆናል፤

ስልክ ቁጥር 09-32-08-03-77 ወይም 09-12-05-47-92

የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-10
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-10 15:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስተኛው ቀን 9፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል  አዲስ ሕይወት አክስዮን ማኅበር
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T07:34:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders