የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢ.ኢ.ግ.ል.ድ) የደንበኞች ዕርካታ ጥናት የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የደንበኞች ዕርካታ ጥናት የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
-ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር ሰርተፍኬት፣በመንግስት የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል። ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ የግዥ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የደንበኞች ዕርካታ ጥናት የአገልግሎት ግዥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን፤ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን ዘኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።
ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ 1% (አንድ ፐርሰንት) በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial lnputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ አዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሃንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት)።
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ፡- በስልክ ቁጥር በመደወል ማግኘት ይችላሉ ።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-04 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopia's Industrial Inputs Development Enterprise
- Buyer address: በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሐንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ|ቤት)።
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 24, 2026
- Posted at: 2026-05-25T07:36:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.