የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ሚኒ-ባስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥ ከተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCDE 008/2018

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ሚኒ-ባስ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ግዥ ከተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

1. ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ፣የአገር ውስጥ አምራች ወይም ገጣጣሚ ወይም የአምራች ሀጋዊ ወኪል ማስረጃ (letter of authorization) የገጣጣሚ ህጋዊ ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።

4. ጨረታው ከግንቦት 16 ቀን 2018 እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ አራተኛ ፎቅ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዢ ዴስክ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።

7. ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል።

9. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብር 400,000 (አራት መቶ ሺ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23

አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ አራተኛ ፎቅ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-02 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defence Construction Design Enterprise
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንፃ ፊት ለፊት የቀድሞው ኖሬላ ግቢ ውስጥ
  • Bid bond: 400,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T10:05:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders