የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ብዛት አንድ ባለ 12ቶን ክሬን ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ብዛት አንድ ባለ 12ቶን ክሬን ተሸከርካሪ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ በጨረታ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የግብር ከፋይነት ሰርቲፊኬት (TIN) ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /VAT Register/ የሆኑና
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ወይም ህጋዊ በጊዜ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 27 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ን/የስራ ሂደት ቢሮ (ቢሮ ቁጥር 14) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ተለያይቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል / ቴክኒካልና ፋይናንሻል/ እና አንድ ኮፒ /ቴክኒካልና ፋይናንሻል/ የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- በሀገር አቀፍ በዓላት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት የስራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የስራ ቀን ይቆጠራል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 211 3316/058 112 0697 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።
በጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት
ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-07-31
- Publishing entity: Gonder City Water and Sewerage Service Bureau
- Bid bond: ለእያንዳንዱ የጠቅላላ ዋጋውን 1%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jul 16, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.