ዘመን ባንክ አ.ማ. ቼይን ኤክስካቫተር ማሽን ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ዘመን ባንክ አ.ማ. ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን ቼይን ኤክስካቫተር ማሽን ባለበት ሁኔታ (AS IS) በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተበዳሪው ስም

የአስያዡ ስም

የሠሌዳ ቁጥር

የሞተር ቁጥር

ሲሪያል ቁጥር

የተሰራበት ዘመን

የንብረቱ ዓይነት

የሐራጅ መነሻ ዋጋ

ሐራጅ የሚከናወንበት

ቀን

የምዝገባ ሰዓት

የጨረታው ሰዓት

 አቶ ንዋይ ብርሃኑ አስፋው

/ ሜላት ዮሐንስ

አቶ ንዋይ ብርሃኑ አስፋው

/ ሜላት ዮሐንስ

ሥከ-EX-2507

BD402828

CAT0330DASZK00537

2016

ቼይን ኤክስካቫተር CAT330D2L

ብር 3,288,552.39 (ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር 39/100)

ሰኔ 4 ቀን 2018 .

 ጠዋት

400-5.30

 

ጠዋት

5.30-6.20

 


የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የንብረቱን የመነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በዘመን ባንክ አ.ማ ስም በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. አሸናፊው/ዋ የሚለየው በደብዳቤ ሲገለጽ ነው፡፡አሸናፊው/ዋ አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለባቸው፡፡ይህንን ካላደረጉ ያስያዙት ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ እንደገና ጨረታው ይካሄዳል፣ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።
  3. ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው።
  4. ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ቀረጥም ካለ በሙሉ በጨረታው አሸናፊ/ዋ የሚከፈል/የሚከፍሉ ይሆናል።
  5. አሸናፊው/ዋ ያሸነፉበት ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የመክፈል ግዴታ አለባቸው ።
  6. የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኃላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም፣ ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም፡፡ይህንን ደንብ የማያከብር እና ጨረታውን የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል።
  7. ባንኩ ማሽኑ በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡ ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያ ገዥው ይከፍላል።
  8. የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው በባንኩ ሚዛን አማን ቅርጫፍ ነው።
  9. ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጠውን ማሽን መጎብኘት ይችላሉ።
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-5-572535 ወይም 0911152490 ወይም 0911456203 ወይም 0919 60 26 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዘመን ባንክ አ.ማ.
Mexico, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212    Addis Ababa, Ethiopia


Tender details

  • Deadline: 2026-06-11
  • Bid closing time: 12:20
  • Bid opening: 2026-06-11 12:20
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Zemen Bank S.C.
  • Buyer TIN: 0004608547
  • Buyer address: Josef Tito Street
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T12:58:04.000Z
  • Buyer website: https://www.zemenbank.com

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders