የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከክልሉ መንግስት በተፈቀደለት ካፒታል በጀት ጄኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይደፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከክልሉ መንግስት በተፌቀደለት ካፒታል በጀት ጄኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር የከፈለና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ
- ጄኔሬተር ለመፈፀም በቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒክና የፋይናስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፕ የውጭ ገጽ ዋና ኦርጂናል/ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በማንኛውም ኤንቨሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም ስለ ተጫራቾች የንገድ ፈቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቨሎኘ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው ኦሪጅናል / ሆነ ኮፒ ኤንቨሎኘ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፣
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምር ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ 8:00 ድረስ ብቻ ሊሆን ጨረታዉ የሚከፈተው በእለቱ 8:30 ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል። የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥስው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በአፌዴሪ/ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለብቻ በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈልገ ተጫራች ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጦ መጫረት ይቻላል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 0467710849 ስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ።
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የጄኔሬተር ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተያያዘና የተገለጽ በመሆኑ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
የቢሮ አድራሻ፡- በስልጠ ዞን ወራቤ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ ጎን።
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክሎጂ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-06-08
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-08 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ 8:30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Science and Information Technology Office of Central Ethiopian Regional Government
- Bid bond: 2%
- Published: May 24, 2026
- Posted at: 2026-05-25T14:14:15.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.